Friday, October 14, 2016

ወይ ፍቅር...!

አንድ ወጣት ፍቅረኛውን ሞተር ሳይክሉ ላይአፈናጦ በሰአት160 ኪሎ ሜትር ይከንፋል።
ልጅት፦ እባክህ ፍጥነት ቀንስ የኔ ፍቅር ፈራሁ እኮ ልጅ፦ እንድንዝናና ብዬ ነው
ልጅት፦ ኖ ፍቅር በጣም አስፈሪ ነው፤ ፕሊስ
ፍጥነት ቀንስ
ልጅ፦ እሺ እንድቀንስልሽ እንደምትወጂኝ ንገሪኝ
ልጅት፦ አፈቅርሀለሁ የኔ ቆንጆ። እሺ አሁን ቀንሰዋ
ፍቅር ልጅ፦ ሳም አድርጊኝና
ልጅት፦ ወገቡን እንቅ አርጋ እንደያዘች ሳምምምም አደረገችው
ልጅ፦ በጣም ስለሞቀኝ ሄልሜቴ ደሞ አንሺልኝና አንቺ አጥልቂው አላት። እንዳላት አደረገች።
በማግስቱ አንድ የአገሬው ጋዜጣ እንዲህ የሚል ዜና ይዞ ወጣ 
''አንድ ሞተር ሳይክል በፍሬን ብልሽት ምክንያት ተጋጭቶ ሞተሩን ሲያሽከረክር በነበረው ወጣት ላይ የሞት አደጋ ሲከሰት አብራው
የነበረች ፍቅረኛው ግን ተርፋለች።
ለካ...
ሞተሩን ያሽከረክር የነበረው ፍቅረኛዋ ድንገት ፍሬን እንደተበላሸበት ሲገባው እሷ እንዳታውቅ በማድረግ የመጨረሻ የፍቅር ቃሏን ተቀብሎ፣ የስንብት በከንፈሯ ተስሞ፣ ሄልሜቱን እሷ እንድታጠልቅ አድግርጎ፣ እሷ በህይወት
እንድትኖር ራሱን ለመስዋዕትነት እያዘጋጀ ነበር !!! እንደዚ አይነት ፍቅር ይስጠን!!!

Share:

0 comments:

Post a Comment

ጣዕም

Featured

ፍ ቅ ር