ጠቅላላ ዕውቀት

                                                                      ወርቅ

ወርቅ ከማንኛውም ብረት ይበልጥ በቀላሉ የሚፈለገውን ቅርፅ ሊሰጥ የሚችል ማዕድን ነው::

ወርቅን ማይክሮ ሜትር እስኪያህል ድረስ ማሳነስ ይቻላል::

28 ግራም የሚመዝነውን ወርቅ በመጠፍጠፍ 17 ካሬ ሜትር ቦታ እስኪሸፍን ማቅጠን ይቻላል::
28 ግራም ወርቅ እንደ ክር እየተጎተተ 70 ኪሎ ሜትር ድረስ ሊረዝም ይችላል::

ንፁህ ወርቅ ጥንካሬ ስለሚጎድለው ከሌሎች የብረት አይነቶች ጋር ተጠቅልሎ እንዲጠነክር ይደረግና የተለያዩ ጌጣጌጦች ይሰሩበታል::

የወርቅ የጥራት መጠን የሚገለፀው በአንድ ሀያ አራተኛ (1/24ኛ) መለኪያ ሲሆን ይህም ካራት ይባላል::
- በመሆኑም 12 ካራት ወርቅ ማለት 50 በመቶው ወርቅ ነው ማለት ነው::
- 18 ካራት ደግሞ 75 በመቶ ወርቅ ነው::
- 24 ካራት ከሆነ ደግሞ ንፁህ ወርቅ ነው::

በዓለም ግንባር ቀደም ወርቅ አምራች አገሮች ደቡብ አፍሪቃና ዩናይትድ እስቴት ናቸው::

→ → መዝናኛና መረጃ (infotainment)
ዕንቁ ህዳር 2005 ዓ.ም




 ታዋቂ የንግድ ስሞችና የስያሜያቸው አነሳስ
ወዳጆቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት?!
እርሶ የሚያውቁትን ጨምሩበት?!
ደስ የሚል ቀንና ጫፋጭ ምሽት ተመኝተናል!

• ናይክ - ከግሪክ የድል አማልክት ስም የተገኘ
• ኖኪያ - ፊንላንድ ውስጥ ከሚገኘው ኖክያ የወረቀት ፋብሪካ የተወሰደ
• ፊሊፕስ - ኤንተን ፊሊፕስ ከተባለ የተባለ የባለሙያ ስም የተገኘ
• ሱዙኪ - በመስራቹ ሚችዬ ሱዙኪ ስም የተወሰደ
• ፎርድ ሞተር - መስራች ሄነሪ ፎርድ ናቸው
• ሂታቺ - የጠዋት ጀምበር ማለት ነው
• ሆንዳ - መስራች ሲቾሮ ሆንዳ በመሆኑ ነው
• አይ.ቢ.ኤም - ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ማን ማለት ነው
• ጂቪሲ - የጃፓን ቪክተር ካምፓኒ አህፅሮተ ቃል
• ኪያ ሞተር - ኪ-ያ ማለት ‹‹ከእስያ የተነሳ›› ማለት ነው
• ኮኒካ - የኮኒ ሺሮኩ ካጋኩ አጭር አፃፃፍ
• ላዳ - የስላቪክ አማልክት ስም
• ኤል ጂ (LG) - ላኪ (Lucky) እና ጎልድ ስታር (Gold star) መነሻ ቃላት
• ማርቼዲስ - ኤሚል ጂሊከን የተባለ መኪና አከፋፋይ ባለሀብት ሴት ልጅ ስም የተወሰደ
• አዲዳስ - የካምፓኒው መስራች Addolf Dassler (Adi + Das)
• ቢ.ኤም.ደብሊው - የባቫሪያን ሞተር ወርክስ አጭር አፃፃፍ
• ዴል - መስራች ማይክል ዴል በመሆኑ
• ፊያት - Fabbrica Italiana Automobil Torino (FIAT)

→ → ከእውቀት ማህደር ቁጥር ሁለት መፅሐፍ የተወሰደ ዶ/ር ኬኬ



 እውቀት ከኦሎምፒክ መንደር!
ወዳጆቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት?!

ከትናንት ቀጠልን:: እንደተለመደው እኛም ገፃችን ላይ ጠቃሚ የምንለውን እንለጥፋለን እናንተም አንብባችሁ ስትጨርሱ ለወዳጆቻችሁ እንዲደርስ ተጋሩት! እንዲህ እንዲያ እያልን እውቀት እንቀባበላለን::
መልካም ንባብ ከጣፋጭ ግዜ ጋር ተመኝተናል::


* የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪቃዊ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ አበበ በቂላ ነው!
* የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪቃዊ የወርቅ ተሸላሚዋ ሴት ደራርቱ ቱሉ ናት!
* የመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪቃዊ የማራቶን አሸናፊ ፋጡማ ሮባ ናት!
* የ12 ዓመቱ ዴንማርካዊ ኢንግ ሶረሰን በ200 ሜትር ዋና የነሀስ ሜዳልያ አሸናፊ በመሆን አለምን አስደምሞል!
* በእድሜ ትልቁ የኦለምፒክ ተወዳዳሪ እንግሊዛዊው ሌርና ጆንስቶን ሲሆን በ1972 የፈረስ እሽቅድምድም ሲወዳደር እድሜው 70 ዓመት ነበር::
* የሶቭየት ህብረት ማርያ ጎሮኮቭካዮ በኦለምፒክ ላይ 2 ወርቅና 5 ብር ሜዳልያ በማግበስበስ የእንስቶችን ሪከርድ ይዛለች::
* በደቡብ አሜሪካና በአፍሪካ ውስጥ ያለ የትኛውም ሀገር ኦሎምፒክን አዘጋጅቶ አያውቅም::
* በ1896 የመጀመሪያው ኦሎምፒክ ላይ አንደኛ ለወጣው የተሰጠው ሽልማት የብር ሜዳልያ ሲሆን ለሁለተኛው ደግሞ የነሀስ ሜዳሊያ ነበር:: በዚህ ኦሎምፒክ ላይ አንዳችም የሴት ተወዳዳሪ አልነበረም::
* በ1900 የፓሪስ ኦሎምፒክ ላይ ከነበሩት ውድድሮች አንዱ አሳማን በጥይት አነጣጥሮ መምታት ነበር::
* የኦሎምፒክ መሪ ቃል "ሲተስ አስተስ ፎርትየስ" ሲሆን ትርጉሙም "ፍጥነት ከፍታና ጥንካሬ" ማለት ነው:

* ስልክ ፈጣሪው አሌክስአንደር ግርሀም ቤል ለሚስቱም ሆነ ለእናቱ ስልክ ደውሎ አያውቅም:: ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ሁለቱም መስማት የተሳናቸው መሆናቸው ነው::
* ድመቶች ከመቶ በላይ የተለያየ ድምፅ ማውጣት የሚችሉ ሲሆን ; በአንፃሩ ውሻ ማውጣት የሚችለው ድምፅ አስር ብቻ ነው::
* አልበርት አንስታይን እና ቻርልስ ዳርዊን ሁለቱም የአክስታቸውን ልጅ ነው ያገቡት::
* የጣት መገጣጠሚያዎችዎን ሲያጮሁ የሚሰሙት ድምፅ የናይትሮጂን ጋዝ አረፋ ሲፈነዳ የሚያሰማውን ድምፅ ነው::
ናፖሊዮን ሂትለር
* ናፖሊዮን በ1760 ተወለደ:: ሂትለር ደግሞ በ1889:: ልዩነቱ 129 አመታት ነው::
* ናፖሊዮን በ1804 ወደ ስልጣን ወጣ:: ሂትለር ደግሞ በ1933:: ልዩነቱ አሁንም 129 አመታት ነው::
* ናፖሊዮን ሩሲያን በ1812 ወረረ:: ሂትለር ደግሞ በ1941:: የዚህም ልዩነት 129 አመታት ነው::
* ናፖሊዮን በ1816 ተሸነፈ:: ሂትለርም በ1945 የሽንፈት ፅዋ ጨለጠ:: ልዩነቱ 129 አመታት ነበር:: ይህንን ምን እንበለው? አጋጣሚ ወይስ . . . ?


 ጃፖን ፤ Japan
ወዳጆቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት!?

• የጃፓን ህፃናት ተማሪዎች በየቀኑ ለ15 ደቂቃ ከመምህራኖቻቸው ጋር በመሆን ትምህርት ቤታቸውን ያፀዳሉ፡፡
• ጃፓን የተፈጥሮ ሀብት የላትም፡፡ ይባስ ብሎም በመቶዎች በሚቆጠሩ የመሬት መንቀጥቀጦች በየአመቱ ትመታለች፡፡ ነገር ግን በ ሀብት ከመጀመሪያዎቹ ሶስቱ ኃያላን ከመመደብ ማንም ያገዳት የለም፡፡
• በጃፓን የጽዳት ሰራተኞች ‹የጤና መሀንዲስ› በመባል ሲጠሩ ፤ አንድ የፅዳት ሰራተኛ በወር ከ 5000 – 8000 የአሜሪካ ዶላር ተከፋይ ነው፡፡
• ጃፓን ከበለፀጉት ሀገራት ብትመደብም የቤት ውስጥ አገልጋይ(የቤት ሰራተኞች) ግን የሏቸውም፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ወላጅ ስለ ቤቱና ስለ ልጆቹ ትልቅ ኃላፊነት ስላለበት፡፡
• ጃፓኖች በግዜ አጠቃቀምና ቀጠሮ አይታሙም ፤ ለደቂቃና ሰኮንዶች ጠንቃቆች ናቸው፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆን አስገራሚ ሁነት እንንገራችሁ፡፡ በአመት በጃፓን በባብሮች ላይ የሚከሰቱ መዘግየቶች ቢደመሩ ከሰባት ሰኮንድ አይበልጥም፡፡ ሰባት ሰኮንድ በአመት!
• የጃፓን ህጻናት ተማሪዎች ምግብ ከተመገቡ በኋላ ጥርሳቸውን እንዲያፀዱ ይደረጋሉ፡፡ ከህፃንነታቸው ጀምረው ለጤናቸው ጠንቃቆች እንዲሆኑ በማሰብ፡፡


 አስገራሚ ከተማዎች!
ወዳጆቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት!?

1. Nauru - የብዙሀን ወፍራሞች መኖሪያ!
በ Nauru ደሴት ከሚገኙ ህዝቦች መካከል ከ 95% በላይ ህዝብ ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው ናቸው፡፡

2. Canada - የሀይቆች መናኸሪያ!
በ Canada ወደ ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሀይቆች ይገኛሉ፡፡

3. Mongolia - ጎረቤት ናፋቂዎች!
በአማካይ በ Hong Kong በአንድ ስኩዌር ማይል ስፋት ውስጥ 340,000 ሰው ሲገኝ ፤ በ Mongolia ግን በአንድ ስኩዌር ማይል ስፋት ውስጥ 4 ሰው ብቻ ይገኛል፡፡

4. Saudi Arabia - ወንዝ ናፋቂዋ!
Saudi Arabia ምንም ወንዝ የላትም፡፡ አብዛኛውን ንፁህ ውሀ የምታገኘው ከከርሰ ምድር (ground water) ነው፡፡

5. Niger - የታዳጊ ልጆች ሀብታም!
በ Niger ግማሽ የሚያህለው ህዝብ (49%) ከአስራ አምስት አመት በታች ያለ ታዳጊ ነው፡፡

6. Papua New Guinea - ብዙ ቋንቋ የሚነገርባት!
እንግሊዘኛ ብሔራዊ ቋንቋ ቢሆንም ከ1-2% የሚሆነው ህዝብ ብቻ እንግሊዘኛን መናገር ይችላል፡፡ አስገራሚው ነገር በPapua New Guinea ከ820 በላይ ቋንቋ መነገሩ ነው፡፡ ይህም በዓለም ላይ ካሉት ወደ 12 % እንደማለት ነው፡፡

7. Canada - የብዙ የተማረ ህዝብ መኖሪያ!
50% ካናዳዊያን ምሩቃ ሲሆኑ ፤ እስራኤል 45% ጃፓን ደግሞ 44% ይከተሏታል፡፡


 • 40% የሚሆኑ ጎልማሳ አሜሪካዊያን በ theory of evolution ያምናሉ፡፡
• 69% አሜሪካዊያን ኢንተርኔት ይጠቀማሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ 5.5% ብቻ ህንዳዊያን ኢንትርኔት ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡
• በአፍሪካ ከ 16 እናቶች አንዷ፡፡ በእስያ ከ65 እናቶች አንዷ እንዲሁም በአውሮጳ ከ 1400 እናቶች አንዷ በወልድ ምክንያት ትሞታለች፡፡ በአመት 500,000 እናቶች ይሞታሉ፡፡ (በደቂቃ አንድ እናት ገደማ!)
• በምድር ላይ 10,000 አይነት የአዕዋፋት ዝርያዎች አሉ፡፡
• ወፎች ከፍተኛ የልብ ምት አላቸው፡፡ በእረፍት ላይ እያሉ ልባቸው በደቂቃ 400 ያህል ግዜ ሲመታ : ሲበሩ ደግሞ ወደ 1000 ይደርሳል፡፡

--- የዓለም ህዝብ ቁጥር ---
• 1800 የዓለም ህዝብ ቁጥር 1 ቢሊዮን ነበር፡፡
• 1930 የዓለም ህዝብ ቁጥር 2 ቢሊዮን ነበር፡፡ (በ 130 ዓመት እጥፍ ሆነ )
• 1999 የዓለም ህዝብ ቁጥር 6 ቢሊዮን ነበር፡፡ (በ70 ዓመት ውስጥ በ4 ቢሊዮን አደገ)
• 2012 የዓለም ህዝብ ቁጥር 7 ቢሊዮን ነበር፡፡ (በ13 ዓመት ውስጥ በ1 ቢሊዮን ጨመረ)

?እናስ 8 ቢሊዮን መቼ እንሞላ ይሆን?


 ወዳጆቻችሁ እንዲያነቡት ተጋሩት!?

• ዱባይ የዐረብ ኤሜረትስ ሁለተኛ ትልቋ ከተማ ስትሆን ከአጠቃላይ ነዋሪዎች 80 % የውጭ ዜጋ ነው፡፡
• በ1968 ዓ.ም በዱባይ ውስጥ ነበሩ የመኪናዎች ቁጥር 13 ብቻ ነበር፡፡
• ሐዋይ ውስጥ ዋይ አሌ በተባለ ተራራ ላይ በዓመት 360 ቀናት ይዘንባል፡፡
• በአይስ ላንድ ውስጥ በየአመቱ ከሚሰጠው የዪኒቨርስቲ ድግሪ 2/3ኛውን የሚቀበሉት ሴቶች ናቸው፡፡
• ከእንጆሪ ይልቅ በሎሚ ውስጥ ብዙ የስኳር መጠን አለ፡፡
• ስፔን የሚለው ቃል ትርጉሙ የጥንቸሎች ሀገር ማለት ነው፡፡
• በየዓመቱ በህንድ ውስጥ አዲስ የሚወለደው ህፃን ቁጥር በአውስትራሊያ አህጉር ውስጥ ካለው ህዝብ ብዛት ይበልጣል፡፡
• ዚምባብዌ ማለት በሾና ቋንቋ ‹‹ትልቅ ድንጋይ ቤት›› ማለት ነው፡፡
• በአለም ላይ የመጀመሪያው የኮምፒውተር ቫይረስ የተሰራው በፓኪስታን ሀገር ሲሆን ስሙም ብሬይን ወይም ጭንቅላት የሚል ነበር፡፡
• በጀርመኖች ባህል በሰርግ ወቅት ሙሽራው መልካም እድል እንዲገጥመው ተብሎ በኪሱ ውስጥ ዳቦና ጨው ይይዛል፡፡


 • በ1992 የኢትዮጲያን ብሔራዊ መዝሙር ዜማ ያዘጋጀው ደረጀ መላኩ ሲሆን ፤ ግጥሙን የፃፈው ሰለሞን ሉሉ ይባላል፡፡ የመዝሙሩም ስያሜ ‹‹ወደፊት ገስግሽ ውድ እናት ኢትዮጲያ›› ይባላል፡፡
የዜግነት ክብር በኢትዮጲያችን ፀንቶ . . . . .
• የኢንዶኔዥያ ብሔራዊ መዝሙር ‹ራያ› ይባላል ትርጉም ‹‹ታላቋ ኢንዶኔዥያ›› ማለት ነው፡፡
• የኢራቅ ብሔራዊ መዝሙር ‹ማውቲና› ይባላል ትርጉም ‹‹የምኖርብሽ ቤቴ›› እንደማለት ነው፡፡
• የሶማሊያ ብሔራዊ መዝሙር ‹ሶማሊያ ቶሶ› ይባላል ትርጉም ‹‹ሶማሊያ ተነሽ›› ማለት ነው፡፡
• የእስራኤል ብሄራዊ መዝሙር የተፃፈው በ1948 ሲሆን ‹‹ሃ ቲክቫህ›› ወይም ‹‹ተስፋ›› ተብሎ ይጠራል፡፡
• የግብፅ ብሔራዊ መዝሙር ‹ቢላዲ ቢላዲ ቢላዲ› ይባላል ትርጉም ‹‹ሀገሬ ሀገሬ ሀገሬ›› ማለት ነው፡፡
• ትምባሆ ጢስ ውስጥ 4000 ኬሚካሎች ሲኖሩ ፤ ቡና ውስጥ ደግሞ 1000 ይገኛሉ፡፡
• ከወር አበባ ጥቂት ቀናት በፊት በሴቶች ላይ ‹‹premenstrual syndrome›› ይከሰታል፡፡ ለዚህ አንድ ፍቱን መድሀኒት ሙዝ መመገብ ነው፡፡
• አስደሳች መዓዘ ያላቸውን ልዩ ልዩ ነገሮችን በማሽተት ህመምን የመፈወስ ጥበብ አሮማቴራፒ ይባላል፡፡
• በእርግዝና ወቅት የሴት ልጅ ማህፀን በፊት ከነበረው ይዘት በ500 እጥፍ ይጨምራል፡፡
• በቻይና ውስጥ 300 ሚሊዮን አጫሾች ያሉ ሲሆን በአንድ ደቂቃ ውስጥ 3 ሚሊዮን ሲጋራ ይጨሳል!





0 comments:

Post a Comment

ጣዕም

Featured

ፍ ቅ ር