አጫጭር ቀልዶች

ሚስት( ትደውልና) የማትረባ! ደደብ! የት አባክ ነው ያለከው?
-ባል፦ ፒያሳ ነኝ!
-ሚስት፦ እዛ ምን ትሰራለሀ?!
-ባል፦አንዴ ትዝ ካለሽ የሆነ ወርቅ ቤት አልጎበኘንም?
-ሚስት፦ አስታወስኩት ውዴ
ባል፦ የወርቅ ሀብል አይተሽ ወደድኩት ስትይ ገንዘብ ሳገኝ
እገዛልሻለው አላልኩም?
ሚስት፦አዎ የኔ ፍቅር.
ባል፦ ወርቅ ቤቱን አወቅሽው?
ሚስት፦አዎ ወለላዬ
ባል፦ከእሱ አጠገብ ያለው ግሮሰሪ ነኝ



 የውሸታሞች ሙግት
አንደኛው ውሸታም፤
“የዛሬ 10 ዓመት አባቴ በህንድ ውቅያኖስ ላይ በመርከብ
ሲንሣፈፍ የእጅ ሰዓቱ ወድቆበት ከ10 ዓመት በኋላ ሲመለስ
በዋና ውኃ ውስጥ ገብቶ ሲፈልግ ሰዓቱ ምንም ሳይሆን
እየሠራ አገኘው ይለዋል”
ሁለተኛው ውሸታም፤
“ይገርምሃል የኔም አባት በዚሁ ውቅያኖስ ላይ ሲንሳፈፍ ወድቆ
ከ10 ዓመት በኋላ ምንም ሳይሆን በሕይወቱ ዋኝቶ
ወጣ፡፡”
አንደኛው ውሸታም፤
“እንዴት ያንተ አባት ሳይሞቱ ውኃ ውስጥ ሊኖሩ ቻለ፡፡ደግሞስ
ምን እየሠሩ ይሕን ያህል ዓመት ቆዩ” ብሎ ይጮህበታል፡፡
ሁለተኛው ውሸታም፤
“ውኃ ውስጥ እንኳን ሳይሆን አሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ነው
የቆዬው፣ ብቻ አንዳንድ ጊዜ ያንተን አባት ሰዓት እንዳይቆም
እየወጣ ይሞላ ነበር ሲል መለሰለት፡፡
--------------- ------
Round 2
አንደኛው ውሸታም፤
“የኔ አባት በርሻው ቦታ ላይ አውሮፕላን የሚያህል ጥቅል
ጐመን አምርቶ አንደኛ ወጣ፡፡
ሁለተኛው ውሸታም፤
“የኔም አባትኮ በጋራዣችን ውስጥ ትልቅ አፍሪካን የሚያህል
ብረት ድስት አምርቶ ተሸለመ፡፡”
አንደኛው ውሸታም፤
“እንዴት! አፍሪካን የሚያህል ብረት ድስት ምን ያደርግላቸዋል?
ብሎ ጠየቀው፡፡
ሁለተኛው ውሸታም፤
“ታዲያ! ያንተ አባት ጥቅል ጐመን በምን ይቀቀላል ሲል
መለሰለት፡፡”



 እሷ: ስንጋባ ጫት መቃምህን ታቆማለህ.
እሱ: እሺ
እሷ: ሲጋራም ማጨስ አትችልም
እሱ: እሺ
እሷ: የሰካራም ሚስት እንድባልም አልፈልግም ስለዚህ
መጠጥም ማቆም አለብህ
እሱ: እሺ
እሷ: ኧ!!! ...ሌላ ደሞ ምን ነበር?? አዎ! እያመሸህ መግባት
አትችልም
እሱ: እሺ
እሷ: እም...ሌላ? ሌላ? ምንድነው የረሳሁት??? ሌላ
የምትተወው ነገር ምን ነበር???
እሱ: አንቺን ማግባት


 ሚስት አምሽታ ወደቤት እየገባች ነው ...
ወድያው የመኝታ ቤቷን ከፍታ ስትገባ
አልጋዋ ላይ ሁለት የተኙ ሰዎችን
ትመለከታለች፤ አራት እግሮች ከብርድ ልብሱ
ስር ወተው ይታያሉ
ከዝያም ወድያውኑ አጠገቧ ያለውን ዱላ አንስታ
ከብርድ ልብሱ ውስጥ ያሉትን ሁለቱን ሰዎች
ባላት ኃይል መደብደብ ትጀምራለች ..ወድያው
መደብደቡን ታቆምና ወደ ሳሎን ቤት ስትሄድ
ባሏ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ጋዜጣ ያነብ ነበር
ከዝያም ባልየው " hi darling...ቤተሰቦችሽ
መተዋሉ
የኛ መኝታ ቤት ተኝተዋል ሰላም አልሻቸው ..?
ሲላት ሚስት በድንጋጤ እራሷን ስታ ወደቀች ::
"የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አሉ"



 Love In A Digital Age
ጎግዬ አስጎግዬ ያን ሰሞን ያጣኋት
አወይ አጋጣሚ CHAT ላይ አገኘኋት
ADD ያረኳትን ልጅ አምናና ካቻምና
አየኋት FACEBOOK ላይ ያቻትና ያቻትና
ONLINE አየናት ሲሉኝ ትላንትና
FACEBOOK LOGIN ብዬ አጣኋት ሄድኩና
አገኛት እንደሆን TWITTER ላይ ሄድኩኝ
አይኔ እንደናፈቃት ሳላያት አደርኩኝ
YOUTUBE ገብቼ SEARCH አድርጌ አጣኋት
TODAY እንደ ድንገት FACEBOOK ላይ አየኋት
ጎግዬ አስጎግዬ ዛሬ አጊንቻታለሁ
CHAT አድርጊው በሏት እኔ እሻላታለሁ



 አለቃ ገብረ ሃና ከዕለታት አንድ ቀን መንገድ እሄዳለሁ ብለ ይነሣሉ፡፡ “ማዘንጊያ” ይላሉ ሚስታቸውን “አቤት” ይላሉ ሚስት “መንገድ ልሄድ አስቤያለሁ” “ወዴት?” “ወደ ቆላ ወርጄ የታመመ ጠይቄ፣ የተጣላ አስታርቄ እመለሳለሁ!” “እንግዲያው ባዶ ሆድዎን አይሄዱም ቆይ ቁርስ ደርሷል፡፡” “ባዶ ሆዳችንን አደል የተፈጠርን? “ቢሆንም ወንድ ልጅ የሚገጥመው ስለማይታወቅ ባዶ ሆዱን አይወጣም” “ሴትስ የሚገጥማት ታጣለች ብለሽ ነው? ካልሽ እንግዲህ ቶሎ አቅርቢልኝና ፀሃዩ ሳይገርር ልነሳ” ወ/ሮ ማዘንጊያ ጉድ ጉድ ብለው ቁርስ አቀረቡና አብረ በልተው ተሰነባብተው ተለያዩ፡፡ አለቃ ቆላ ወርደው የታመመ ጠይቀው የተጣሉትን ሁለት ሰዎች ሊያስ...ታርቁ ግቢያቸው ሲደርሱ ጭራሽ ተጋግለው ቡጢ ሊቀማመሱ ግራ ቀኝ ሲሉ ያያሉ፡፡ ሰዎቹ አንደኛው የተማረና አዋቂ የሚባል ሰው ነው፡፡ ሌላኛው ምንም ያልተማረ መሀይም ነው፡፡ መሀይሙ የተማረውን፡ “አንተ ደንቆሮ! ዶሮ ራስ!” ይለዋል፡፡ “አፍህን ዝጋ ነግሬሃለሁ!” ይላል የተማረው “ደንቆሮ! ደደብ! ቆርቆሮ!” ይላል መሀይሙ፡ “ምንም ልሁን አፍህን ካልዘጋህ ዋጋህን ታገኛለህ!” አለቃ፤ “ተው እንጂ ተው አይሆንም!” ይላሉ ሊገላግ መካከል ገብተው፡፡ መሀይሙ አሁንም “ደንቆሮ! አለቃ፤ ይሄኮ ደደብ ነው! ይላል፡፡ አለቃ፤ ሁለቱንም በተለያየ አቅጣጫ ገፍተይለያዩዋቸዋል፡፡ ይሄኔ አንድ መንገደኛ ድንገት ይደርሳል፡፡ አለቃ ያውቃቸዋል፡፡ ወደሳቸው ቀረብ ብሎ፤ አለቃ ምን እያደረጉ ነው?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡ አለቃም፤ “ስድብ ቦታውን ስቶብኝ፤ ቦታ ቦታው እየመለስኩ ነው!” አሉ፡፡

 የ80 ዓመት አዛውንት ለጠቅላላ የጤና ምርመራ (Checkup) ሆስፒታል ይሄዱና ሃኪማቸው “እንዴት ነው ጤንነትዎ?” ሲል ይጠይቃቸዋል፡፡
ሽማግሌውም “በጣም ጤና ነኝ ---እንደውም የ18 ዓመት ኮረዳ አግብቼልህ አርግዛልኛለች----ልጅ ላገኝ ነው --- መታደል ነው አይደል?” ይሉታል - ለሃኪሙ፡፡ ሀኪሙ ነገሩ አልተዋጠለትምና ትንሽ ሲያስብ ከቆየ በኋላ “አንድ ታሪክ አስታወሱኝ” በማለት ይነግራቸዋል፡፡
“አንድ እኔ የማውቀው አደን የሚወድ ሰውዬ ነበር፡፡ በቃ የአደን ነገር ጨርሶ አይሆንለትም፡፡

አንድ ቀን ለአደን ሲወጣ ታዲያ ጠብመንጃውን አነሳሁ ብሎ ዣንጥላውን ይዞ ይወጣል፡፡ ገና ጫካ ውስጥ እንደገባም ከየት መጣ ሳይባል አንድ የተበሳጨ ድብ ፊትለፊቱ ገጭ ይልበታል፡፡ ከመቀፅበት ዣንጥላውን እንደጠመንጃ አስተካክሎ ድቡ ላይ ያነጣጥርበትና እጀታውን ይጫነዋል----ድቡ ወዲያው መሬት ላይ ጠብ ይላል” አላቸው ሃኪሙ፡፡
ሽማግሌውም “ይሄማ ሊሆን አይችልም! ድቡ ላይ የተኮሰው ሌላ ሰው መሆን አለበት!” አሉ - ጮክ ብለው፡፡
ሀኪሙም “የእርስዎም ነገር እኮ እንደዚያ መስሎኝ ነው” አላቸው፡፡



 “የባል ኑዛዜ”

ባል ጣዕረ-ሞት ይዞት እያጣጣረ ሳለ ሚስቱን ያስጠራና “እንግዲህ እኔ መሞቴ ነው፤ አንቺ ግን ያለ ባል መቅረት የለብሽም፤ እንዲያውም ያንን ኩራባቸውን አግቢ” ይላታል። በዚህ አባባል የተናደደችው ሚስት “አንተን ይማርልኝ እንጂ እኔ አሁን ስለ ባል አላስብም! ደግሞ ባገባስ እንዴት ያንተን ዋነኛ ጠላት ኩራባቸውን አግቢ ትለኛለህ?” ስትል ትጠይቀዋለች። በዚህ ጊዜ ጣር የያዘው ባል እያቃሰተ መለስ ብሎ “አንቺ ደሞ አይገባሽም እንዴ? ጠላቴ መሆኑንማ መች አጣሁት? ልክ እንደ እኔ አንገብግበሽ እንድትገድይልኝ ነው እንጂ! አላት ይባላል። ኑዛዜ ይልሃል ይህ ነው! ከእንዲህ አይነቱ ኑዛዜ ይሰውራችሁ ይሰውረን አሜን አሜን በሉ።



 አንድ ሰካራም ለሚስቱ ይደውልና “መኪናዬን
መርካቶ አቁሜ ፣ ሌቦቹ አወላልቀው
ወሰዱት” አላት... “ምን ማለትህ ነው?”..
“በቃ ምንም አልተረፋቸውም! መሪው ፣
ሬዲዮኑ ፣ ምን አለፋሽ? ፊት ለፊት ያለው
ቦርዱን ጭምር ነው የዘረፉኝ።
እነዚህ ቅማላሞች! ፍሬኑና የቤንዚን
መስጫው እንኳን አልቀራቸውም”...
“እሰሰሰሰይ! ደግ አደረጉ! እየሰከሩ ማምሸት
ይቅርብህ ብዬህ አልነበረም!” ስትል ፤ ከት
ብሎ መሳቅ ጀመረ። “ምን ያስቅሃል?”...
“ይቅርታ! ለካ በኋላ በር ገብቼ ነው”


















 ልጅቷ በማታ ወደ ልጁጋ ትደውላለች

''እባክህ ሰሞኑን አንድ እረፍትና እንቅልፍ የነሳኝን ነገር ልጠይቅህ
ምናልባት ጥያቄው ሊከብድህ ይችላል(ልጁ ደንግጧል!!!) ምናልባት ደግሞ ከዚህ በኃላ ስለኔ የተለየ አመለካከት ሊኖርህ ይችላል::ነገር ግን
በቃ ምንም ማድረግ አልችልም አንተ ምን እንደሚሰማህ ማወቅ ስለምፈልግ ነው..(........ፊቱ ላብ በላብ)በጣም ለረጅም ጊዜ ለመጠየቅ ፈርቼ በውስጤ አምቄው ኖሪያለው አሁን ግን ይበቃኛል..በቃ ከራስህ አንደበት ማወቅ አለብኝ እኔ ከዚ በላይ መጎዳት የለብኝም..(ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ነው) ብቻ አንተ ምንም ይህል ከባድ ቢሆን እውነቱን
ንገረኝ እኔ ምፈልገው ግልፅ እንድትሆንልኝ ብቻ ነው..
.
.
.
እናንተ ሰፈር በያይነት ስንት ነው?



 አባት ወደቤት ሲገባ ሚስቱ ልጃቸውን እየመታችው ያገኛታል

አባት፡-" ለምንድነው የምትመችው? ምን አደረገ?"

ሚስት፡- "ይሄ ደደብ 1x1 ስንት እንደሆነ አያውቅም!"

አባት፡- "እና ለዛ ነው እንዲ ምትደበድቢው? አንቺ ታውቂያለሽ ስንት ነው 1x1?"

ሚስት፡- "11"

አባት፡- "በይ ተረፍሻል:: ብትሳሳቺ ኖሮ የሱን ያህል ነበር የምደበድብሽ"



 አሮጊቷ ለዶክተሩ እይነገረችው ነው
"ዶክተር የሆነ ችግር አለብኝ እሱም ፈሴን መቆጣጠር
አልችልም በቃ በሄድኩበት ሁሉ መፍሳት ነው..በርግጥ ፈሴ ምንም አይነት ድምጽም ሆነ ሽታ የለውም ባይገርምህ ዶክተር አንተ ቢሮ ከገባው ጀምሬ እንኳን 20 ጊዜ ያህል ፈስቻለው ግን አላወክም ምክንያቱም ፈሴ ሽታም ሆነ ድምጽ ስለሌለው ነው::"
ዶክተር: "እቺን ክኒን ውሰዷት እና በሚቀጥለው ሳምንት ተመሱ"
አሮጊቷ ከ ሳምንት በኋላ ተመለሰች
አሮጊቷ:(በቁጣ) ምነው ዶክተር ምን አረኩህ የሰጠህኝን ኪኒን ከዋጥኩ ጀምሮ ፈሴ መሽተት ጀመረ በርግጥ ድምዕ የለውም ቢሆንም በጣም ነው ሚሸተው"'
ዶክተር:"በጣም ጥሩ አፍንጫዎት ተሽሎታል ማለት ነው አሁን ደሞ የጆሮ ልስጦት?



ሰውየው የሚስቱን ድመት በጣም ይጠላ ነበር….አንድ ቀን
ሚስቱ ሳታየው ድመቱን አውጥቶ ለመጣል ይወስናል በጠዋት
ተነስቶም ድመቱን 20 ኪሎሜትር ያህል ራቅ አድርጎ ይጥልና
በደስታ ይመለሳል እቤቱ ሲደርስ ግን ድመቱ ሶፋ ላይ ተኝቶ
ያገኘዋል..
በነጋታው ጠዋት ይነሳና ድመቱን 40 ኪሎሜትር ራቅ አድርጎ
ጥሎት ተመለሰ እቤት ሲደርስ ድመቱ እንደ ትላንቱ ሶፋ ላይ
ተኝቶ ያገኘዋል
በየቀኑ ራቅ ራቅ ወዳለ ቦታ እየጣለው ያመጣል ድመቱ ግን
ሁሌም ቀድሞት እቤት እንደገባ ነው::
በመጨረሻም በጣም ይመረውና ድመቱ አያውቀውም ብሎ
ወደሚያስብበት ሩቅ ቦታ ሊጥለው ይወስናል ብዙ
ኪሎሜትሮችን ከተጓዘ በኃላ ወደ ቀኝ ታጠፈ ከዛ ወደ ግራ ከዛ
ወንዙን ተሻግሮ ወደ ቀኝ ድጋሜ ወደ ግራ አሁንም ጥቂት
ተጉዞ ወደ ቀኝ እንዲ እንዲ እያለ የሆነ ቦታ ሲደርስ አሁን
ተገላገልኩ ብሎ ድመቱን ይለቀዋል….
ከሰሀታት በኃላ ሰውየው ሚስቱጋ ደውሎ "ሆዴ ድመቱ አለ
እንዴ?"
ሚስት:" አዎ ምነው….?
"እስቲ አንዴ አቅሪቢልኝ መንገድ ጠፍቶብኛል



 አልኮል ፋብሪካ ውስጥ የነበረ አልኮል ቀማሽ
ይሞትና ማናጀሩ አዲስ ቀማሽ ለመቅጠር
ክፍት የስራ ማስታወቂያ ያወጣል:: አንድ
በጣም የሰከረና ድሪቶ የለበሰ ሰው
ማስታወቂያውን አይቶ ሊፈተን ይመጣል::
ማናጀሩ ገና እንዳየው የሰውዬው ሁኔታ
ይደብረውና ላለመቅጠር ወስኖ ከባድ ጥያቄ
ሊያባርረው ይወስናል:: በብርጭቆ የተሰጠውን
አልኮል ምንነት በመቅመስ እንዲለይ
የመጀመሪያው መጠጥ ተሰጠው:: ሰውየው
መጠጡን ቀመሠና :- *ቀይ ወይን ነው::
*የተሰራው ከነጭ የወይን ፍሬ ነው::
*ከተጠነሰሰ 3 ዓመቱ ነው:: *በደቡብ ሸለቆ
ውስጥ በብረት በርሜሌ የተጠመቀ ነው ሲል
መለሰ:: ማናጀሩ በመልሱ ፍፁም ትክክለኛነት
ተደንቆ ሌላ ብርጭቆ ሰጠው:: ይህንንም
ቀመሠና:- * ከደረቅ ቀይ ወይን የተሰራ ነው::
* ከተጠነሰሰ 8 ዓመቱ ነው:: * በደቡባዊ
ፈረንሳይ *በእንጨት በርሜል የተጠመቀ
ቀይ ወይን ነው" አለ:: ማናጀሩ ገርሞት ቢሮ
ውስጥ የሚያሽኮረምማትን ፀሐፊ ጠርቶ
ያንሾካሹክላታል:: እሷም ወጣ ብላ ሽንቱዋን
በብርጭቆ ይዛ ትመጣና ትሰጠዋለች::
ተፈታኙም ይቀምሰውና:- * ብሎንዲ /ቢጫ
ነገር/ ነው:: * ከተጠነሰሰ 3 ወሩ ነው:: *
የተሠራው ቢሮ ውስጥ ነው:: ካልቀጠርከኝ
ደግሞ አባትዬውንም /የፅንሱንም አባት/
እናገራለሁ ብሎ ቁጭ..



 .አንዱ ከመርካቶ ዶሮ ገዝቶ እቤት ከመመለሱ በፊት እግረ
መንገዱን ሲኒማ ቤት መግባት ፈለገ። ሲኒማ ቤት “ከነዶሮህ
አትገባም” ሲሉት ፣ ይወጣና ዶሮውን ሱሪው ውስጥ ደብቆ
ይገባል። ፊልሙ ሲጀመር ፣ ጨለማን ተገን አድርጎ ፣ ዶሮው
እንዳይታፈን ብሎ ዚፑን ከፈት ሲያደርግ ፤ አጠገቡ
የተቀመጠች ሴት ታስተውልና ፣ ጓደኛዋን ጠጋ ብላ “ወይኔ
ጉዴ! እረ አጠገቤ ያለው ሰውዬ ዚፑን ከፈተው” አለቻት... “
በቃ አትይዋ! የወንድ ብልት እንደሆነ ፣ አንዱን ካየሽ ሁሉንም
አይተሻል ማለት ነው!” ስትላት.... “እሱማ አዎ። ግን ይሄኛው
እኮ ፈንዲሻዬን እየበላብኝ ነው!”


 100 ብርና ተማሪ

አስተማሪ፦ አንተ ምን ሆነህ ነው ያረፈድከው

ተማሪ፦ አንድ ሰውዬ 100 ብር ጠፍቶት ነው::

አስተማሪ፦ ታዲያ አንተ ብሩን
ስታፈላልገው ነበር?

ተማሪ፦ አይ! በእግሬ ብሩ ላይ ቆሜበት ነበር።



 የወንዶች እሮሮ በቀልድ

ባል ከሚስቱ ጋር መርካቶ ሄዶ ሁለቱ የተለያየ ሱቅ ገብተው ተጠፋፉ።

ቢቸግረው አንድዋን ቆንጆ ልጅ ያስቆምና ..."ሚስቴ ስለጠፋችብኝ በናትሽ ትንሽ ግዜ አብረሺኝ ሁኚ"...

"እንዴ?ለምን?" ብትለው... "ሁል ግዜ ከቆንጆ ሴት ጋር
ከሆንኩ ፣ ከየት መጣች ሳትባል ነው ብቅ የምትለው"




ጋባዡ......

አንድ ሰውዬ ፊቱ በደስታ ጥርስ በጥርስ ሆኖ መጠጥ ቤት
ውስጥ ይገባና ደብል ውስኪ ያዛል ::

ከዛም ጮክ ብሎ መጠጥ ቤት ውስጥ ላሉት ሰዎች " ዛሬ
የደስታዬ ቀን ነው ስለዚህ እኔ ስጠጣ ሁሉም ይጠጣ "
ይላል :: ሰዎቹም በጭብጨባና በሁካታ ቤትዋን ሞቅ
አድርገውለት ስለግብዣው ምስጋናቸውን ከገለጹ በውሀላ
ተቀድቶላቸው መጠጣት ይጀምራሉ ::

ከጥቂት ጊዜ በውሀላም ሰውዬው በድጋሚ ደብል አስቀድቶ
አሁንም ጮክ ይልና 'እኔ ስጠጣ ሁሉም ይጠጣ ' ይላል ::
በድጋሚ በጭብጨባ ቤትዋ ሞቅ ትላለች መጠጣቱ
ይቀጥላል :: ለሶስተኛ ግዜም ያን ካደረገ በውሀላ ከኪሱ
ቦርሳውን አውጥቶ "በሉ አሁን እኔ ስከፍል ሁሉም ይክፈል "



 አንድ ሰካራም ሰውየ መንገድ ላይ አጥር ተደግፎ ሽንቱን ይሸናል…ድንገት ዞር ሲል ደንብ አስከባሪ አጠገቡ ቆሞ ደረሰኝ ቆርጦ ይሰጠዋል፡፡

ሰውየው ፡- ምንድ ነው ?
ደንብ አስከባሪው፡- እዚህ ጋር መሽናት 5 ብር ያስቀጣል
ሰውየው ወንጀለኝነት በተሰማው መንፈስ 5 ብር ከ50 ሳንቲም ይሰጠዋል ፡፡
ደንብ አስከባሪው፡-..ሃምሳ ሳንቲሙ የምንድን ነው ?
ሰውየው፡- ፈስቻለው


 አንድ ሰውዬ ሰው ሲዋሽ በጥፊ የሚማታ ሮቦት ገዝቶ ቤቱ ሄዶ
ለመሞከር ለልጁ እንዲህ አለው
አባት> ዛሬ ምን ስትሰራ ዋልክ
ልጅ>ከጏደኞቼ ሳጠና
ቹቹዋዋ ሮቦቱ ልጁን በጥፊ አጮለው
ልጁ>እሺ ፊልም ሳይ ነበር
አባት>ምን አይነት ፊልም
ልጅ>አድቬንቸር
ቹቹዋዋ ሮቦቱ ልጁን በጥፊ አጮለው
ልጅ>እሺ porno ፊልም ሳይ
አባት>እንዴ እኔ ባንተ እድሜ እያለሁ porno ምን እንደሆነ
አላውቅም ነበር
ቹቹዋዋ ሮቦቱ አባትን በጥፊ አጮለው
እናት>HaHaHa ለነገሩ አትፍረድበት ያንተ ልጅ አይደል ባንተ
ወቶ ነው
ቹቹዋዋ ሮቦቱ እናትን በጥፊ አጮላት



 1 ሰካራም ሌሊት 5 ሰዓት ኣካባቢ መርካቶ ላይ 50 ሳንቲም
ይጠፋውና ፒያሳ ላይ
ፍለጋውን ይጀምራል:: መኪናዎችን ኣላሳልፍ ብሎ ሲያሥቸግር
የተመለከተው ፖሊሥ እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል
ፖሊሥ - ምን እየፈለግክ ነው?
ሰካራም - ፍራንክ ጠፍቶኝ ነው
ፖሊሥ - የት ነው ያጠፋሀው?
ሰካራም - መርካቶ ላይ
ፖሊሥ - እና መርካቶ ላይ ጠፍቶህ እንዴት ፒያሣ ትፈልጋለህ?
ሰካራም - ፒያሣ መብራት ስላለ ነው :



 የጠበቃ ውሻ የታሰረበትን ገመድ በጥሶ ከቤት በመውጣት በቀጥታ ወደ አቅውራቢያው ስጋ ቤት ካመራ በኋላ ሙዳ ስጋ በጭቆ ያመልጣል፡፡
በውሻው ድርጊት የበገነው የስጋ ቤቱ ባለቤት በቀጥታ ወደ ውሻው ባለቤት ጠበቃ ቢሮ ካመራ በኋላ የሚከተለውን ጥያቄ ይጠይቀዋል፡፡

“የታሰረበትን ገመድ የፈታ ውሻ ከኔ ስጋ ቤት ስጋ ሰርቆ ቢሄድ የውሻውን ባለቤት የስጋዬን ዋጋ ልጠይቀው እችላለሁ?”

ጠበቃውም በእርጋታ ካዳመጠ በኋላ

“ያለጥርጥር!”
በማለት እርግጠኛ መልስ ይሰጠዋል::

የስጋ ቤቱ ባለቤትም እምቅ ፈገግታ ፊቱ ላይ እየተነበበ በልቡም “ሰራሁልሽ!” እያለ “ዛሬ ጠዋት ያንተ ውሻ ማሰሪውን በጥሶ ግማሽ ኪሎ ስጋ ይዞብኝ ሮጧል፡፡
ስለዚህ 20 ብር ልትከፍለኝ ይገባል፡፡” (የስጋው ዋጋ አዲስ በወጣው የመንግስት የዋጋ ተመን መሰረት ነው!)

ጠበቃውም ያለተቃውሞ ከኪሱ 20 ብር አውጥቶ ይሰጠዋል፡፡ የስጋ ቤቱ ባለቤት በጠበቃው ቅንነት እየተገረመ ሊወጣ ሲል ጠበቃው አስቆመውና አንድ ደረሰኝ ጽፎ...

“አንተም ለኔ የምትከፍለው 100 ብር
አለብህ !” ይለዋል

“የምን መቶ ብር?”

“የህግ ምክር የሰጠሁበት ነዋ”






የእንግሊዛውያን የምንጊዜም ቀልድ

አንዲት ሴት ልጇን ይዛ ባቡር በመሳፈር ላይ እያለች የባቡሩ ሹፌር እንዲህ አይነት አስቀያሚ ልጅ አይቼ አላውቅም ይላታል እሷም በጣም ትበሳጭና ከባቡሩ መሀል ሄዳ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች ከዛም ከተሳፋሪዎች አንዱ ለምን እንደምታለቅስ ይጠይቃታል

ሴትየዋ - ሹፌሩ በተናገረኝ ንግግር በጣም ተበሳጭቼ ነው

ተሳፋሪ - ታድያ ለሱ ነው እንዲህ የምታለቅሽው ሄደሽ ልክ ልኩን አትነግሪውም እስከዛ ጦጣውን ልያዝልሽ ::

አላት ይባላል



 ታሪክን የኅሊት

አበበ ቢቂላ ጣሊያን ሮማ ውስጥ ባለው stadio olimpico ውስጥ በባዶ እግሩ ማራቶን ያሸነፈ ጊዜ...

አንድ የተሸነፈ ሯጭ "ለምን በባዶ እግሩ እንዲሮጥ ፈቀዳችሁለት?" "እሱ እኮ ያሸነፈው ሸክም ስለቀለለት ነው" ብሎ ክስ
በማቅረብ ዳኞቹን ሲጠይቃቸው ጊዜ ምን ብለው መለሱለት መሰላችሁ?
.
.
.
.
.
.
"አንተም ሸክም እንዲቅልልህ ከፈለግህ ለምን
ራቁትህን ሮጠህ አታሸንፍም ነበር?"


ሰውዬው ላዳ ታክሲ ተኮናትሮ ከቦሌ እየመጣ ነው፡፡ ሗላ ወንበር ተቀምጦ እየመጣ እያለ የሚያውቀው ሰው ያይና ታክሲውን እንዲያቆምለት ለሹፌሩ ለመንገር ትከሻውን ነካ ያደርገዋል፡፡ ይሄኔ በቅፅበት ውስጥ ታክሲዋ እንዳልነበረች ሆነች… ትከሻውን የተነካው ሹፌር በድንጋጤ መጮህ ጀመረ… ታክሲዋን መቆጣጠር አቅቶትም አንዴ ወደ ግራ ከዛ ወደ ቀኝ ካንገላታት በሗላ በከባዱ እየተነፈሰ እንደምንም የመንገዱ ጥግ ላይ አቆማት፡፡

ወዲያውም “ሰውዬ ያምሃል እንዴ? ምን ነካህ?” እያለ መነጫነጭ ጀመረ፡፡ በሁኔታው የተደናገጠው ተሳፋሪም ይቅርታ እየጠየቀ ..

“እንደዚህ ትደነግጣለህ ብዬ ፈፅሞ አላሰብኩም ነበር፤ እንድትቆምልኝ ፈልጌ ስለነበር ነው” ብሎ ለማስረዳት ሞከረ::

በመጠኑ የተረጋጋው ሹፌርም “ነገሩስ አንተ አይደለህም ጥፋተኛው፤ ገና ዛሬ ለመጀመርያ ጊዜ ታክሲ ስለያዝኩ ነው የተደናገጥኩት መሰለኝ…”

ተሳፋሪ፡- ኧረ! ከዚህ በፊት ምንድነው ትሰራ የነበረው?

ሹፌር፡- የቀብር አስፈፃሚ ድርጅት ውስጥ ሬሳ በመኪና ማጓጓዝ፡፡



 ‹‹አንድ ጠርሙስ አረቄ . . . !››

በጠጪነቱ የታወቀ የአንድ መሥሪያ ቤት ሠራተኛ ጧት ሥራከመግባቱ በፊት ከቤቱ ጀምሮ ባሉ አንድ አራት መጠጥ ቤቶች
ጎራ እያለ ፉት ይላል፡፡ ማታም እንዲሁ አትለፍ የተባለ ይመስል የደንቡን ሳያደርስ ቤቱ አይገባም፡፡ ይህ ልምዱ እንደማያዋጣው በብዙ ሰዎች ከተነገረው በኋላ አንድ ጧት
ለራሱ ቃል ገባ፣ ሳይጠጣ ቢሮው ገብቶ ሳይጠጣ ቤቱ ለመመለስ፡፡ እናም፣ ምሎ እና ተገዝቶ እኒያን መጠጥ ቤቶች ጧት ላይ እየገላመጠ እና እየረገማቸው አልፎ መሥሪያ ቤቱ
ደረሰ፡፡ በውሳኔው ተደስቶ በሰላም ሲሠራ ከዋለ በኋላ ማታም ወደ ቤቱ ሲመለስ የጧቱኑ ዕርምጃ ወሰደ፡፡ ሳይቀምስ ውሎ ሳይቀምስ በመግባቱ ተደስቶ፣ ‹‹ጀግና ነኝ! ቆራጥ! ለዚህ
ጀግንነቴ አንድ ጠርሙስ አረቄ ይገባኛል በማለት ወደ አረቄ ቤት በረረና አረፈዋ!



 ‹‹ተሜ ተቀምጬ ልስጥህ?››
Funny-if u Understand
አንድ የቅኔ ተማሪ ለእራት የሚሆነውን ቁራሽ ለመለመን ወደ ገጠር ነዋሪዎች /ወደ መንደር/ ብቅ ይልና ‹‹በእንተስማ
ለማርያም ስለ ቸሩ እግዚአብሔር ብለው›› ይልና ይለምናል፡፡

ቁራሽ በሚለምንበት መንደር ‹‹ተቀምጬ›› የሚባል የምግብ ዓይነት ነበርና አንዲት ሴት ወይዘሮ እንጀራ አልጋገረች ኖሮ ‹‹ተማሪ እንጀራ አልጋገርኩምና ተቀምጬ
ልስጥህ?›› ትለዋለች፡፡ ተማሪውም መልሶ ‹‹ኧረ እመይቴ የሚዘክሩኝስ ከሆነ ተኝተውም ቢሆን ቢሰጡኝ አልጠላም››
አላቸው ይባላል፡፡



 “አትደርስበትም” great Answer

አንድ ጥጥ የመሰለ ነጭ ሽበት ያለባቸው አዛውንት ቁልቁል
ሲወርዱ አንድ ወጣት ሊተርባቸው አስቦ “አባባ፣አባባ የቃጫ
ፋብሪካ መንገድ በዚህ በኩል ነወይ?” ብሎ ሲጠይቃቸው፣
እሳቸውም ነገሩ ስለገባቸው “አዎን ልጄ መንገዱስ ይኼው፤
ነገር ግን አንተ አትደርስበትም” ብለው መለሱለት፡፡


 ባል ለሚስት በሞባይል መልዕክት... "ነገ ለስብሰባ ወደ ክፍለ ሃገር ስለምሄድ ከውስጥ የምለብሳቸውን ልብሶች ቅያሬ እና ሸሚዝ እንዲሁም ካልሲ በመካከለኛው ሻንጣ አዘጋጂልኝ::"

ትንሽ ቆይቶ እንደገና ሌላ መልዕክት "ውይ ሳልነግርሽ እረስቼው: ባለፈው የተወዳደርኩበትን ቦታ እኮ አለፍኩ:: የደስ ደስ ያንን የእራት ቀሚስ ገዝቼልሽ እመጣለሁ::"

ሚስት በመልዕክት: "አረ: እስቲ ሙች በለኝ?"

ባል ከእንደገና በመልክት: "አረ ውሸቴን ነው:: የመጀመሪያውን መልዕክት እንደደረሰሽ ለማረጋገጥ ነው::"


 ባል የሰሞኑን የሚስቱ ሁኔታ አልጥምህ ብሎት እንዳይነግራት ትዳራቸውን እንዳያቀዘቅዝ ፈርቶ ሀኪም ለማናገር ፈለገ::

"ዶክተር ሚስቴ የመስማት ችግር ሳይኖርባት አይቀርም:: በግልፅ እንዳልነግራት ደግሞ እንዳታኮርፈኝ ፈራሁ::

" ሀኪሙም ከአምስት ሜትር ርቀት ጀምሮ አንድ ሜትር ርቀት እየቀነስክ አንድ ጥያቄ ጥይቃት እና የችግሩን ክብደት እንለያለን ብሎ መክሮ ይሸኘዋል::

ባልም እቤት እንደገባ ከአምስት ሜትር ርቀት "ውድ, ዛሬ ምሳ ምንድን ነው?" ብሎ ይጠይቃታል:: ምን መልስ የለም::

ከአራት ሜትር ጥያቄውን ደገመ:: አሁንም መልስ የለም:: ከሶስት ሜትር: ከሁለት ሜትር: ተመሳሳይ ሞከረ:: ምንም መልስ የለም::

ከአንድ ሜትር ላይ "ሆዴ, ምሳ ዛሬ ምንድን ነው?" ሲላት..

ሚስት "እህ አንተ ሰውዬ ዛሬ ምን ሆነሃል? አሁን እኮ ስትጠይቀኝ ለአምስተኛ ጊዜህ ነው:: ምስር ወጥ አልኩህ አይደል!"






ከ 18 አመት በታች ይህን ጨዋታ እንዲያነቡ አይፈቀድላቸውም !!!

ልጅቷ አምራና ተውባ ከቤት ልትወጣ ስትል አያቷ አስቆሟትና “ ወዴት ልትሄጂ ነው የኔ ልጅ አሏት”

“ከወንድ ጓደኛዬ ጋር ቀጠሮ አለኝ አያቴ”

“ እንደዛ ከሆነ ማድረግ ስለሚኖርብሽ ጥንቃቄ ልንገርሽ ቁጭ በይ፡፡ እነዚህ ወጣቶ ወንዶች ተንኮለኞች ናቸው ሊያሳስቱሽ ይችላሉ፡፡” አሉ አያትየው የወጣትነት ዘመናቸውን በትውስታ እየተመለከቱ፡፡

“አንዴት አያቴ”

“ መጀመሪያ ከንፈርሽን ሊስምሽ ይሞክራል፡፡ እሱ ደሞ ደስ ይላል፡፡ ግን ፈፅሞ ወደ ከንፈሮችሽ እንዲጠጋ እንዳትፈቅጂለት፡፡”

“አሺ ……”

“ሲቀጥል ደግሞ ጡቶችሽን እያሻሸ’ ስሜት ውስጥ ሊያስገባሽ ይሞክራል፡፡ ይሄም በጣም ደስ ይላል፡፡ ግን እንደዛ እንዲያደርግ እንዳትፈቅጅለት፡፡”’

“አሺ ……”

“ሲቀጥል ጣቶቱን በእግሮችሽ መሀል አስገብቶ ሊነካካሽ ይሞክራል፡፡ በእርግጥ ይሄም ጥሩ ስሜት ይፈጥራል፡፡ ሆኖም ልትፈቅጅለት አይገባም፡፡”

“አሺ ……”

“ ይሄም ሁላ አልበቃ ብሎት አንቺን አስተኝቶ እላይሽ ላይ ሊደሰት ይሞክራል፡፡ ስለዚህ ይሄንንም እንዳትፈቅጅለት ቤተሰባችንን ያዋርዳል፡፡”

ከዛ ልጅቷ ምክሩን ሁሉ ከሰማች በኋላ ወደ ወንድ ጓደኛዋ ሄደች፡፡ በማግስቱ አድራ ስትመለስ ደረቷን ነፍታ በድል አድራጊነት ስሜት እያለከለከች ነበር፡፡

“አያቴ መጀመሪያ ላይ ምክሮችሽን ሁሉ ለመተግበር የሚቻለኝን ሁሉ ብሞክርም ተግባራዊ ማድረግ አልቻልኩም ነበር፡፡

አዘናግቶ ከሳመኝ በኋላ የተፈጠረብኝ
ስሜት ቀጣዮቹን ነገሮች ሁሉ ለማስቆም አስቸጋሪ አድርጎብኝ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ስሞኝ ጡቶቼን አሻሽቶ፣ ፓንቴን አውልቆ አስተኝቶኝ……. ከላይ ሆኖ ቤተሰባችንን
ሊያዋርድ ሲል ምን እንዳረኩ ታውቂያለሽ አያቴ?”

“ ምን አደረግሽ ልጄ”

“ገለበጥኩትና ከላይ ሆኜ የእራሱን ቤተሰቦች
አዋረድኩለት……”

አያትየዋ በድንጋጤ አፍጥጠው ቢመለከቷትም ያለፈውን ሌሊት ገድሏን ከመተረክ
አላቆመችም

“ ……ሌሊቱን ሙሉ እንደፈረስ ስጋልበው አደርኩ….



 ማን በለጠ?

እንግሊዛዊው፣ አየርላንዳዊውና ስኮትላንዳዊው ጩኸት የበዛበትና በጭስ የታፈነ በርካታ ሰዎች የተሰበሰቡበት መጠጥ
ቤት ውስጥ ተቀምጠዋል፡፡

የእንግሊዙ ተወላጅ ‹‹የአገሬ የእንግሊዝ መጠጥ ቤቶች ምርጦች ናቸው፡፡ አንደ ነገር የጠጣ ሰው ሁለተኛውን በነፃ ይጋበዛል!›› አለ፡፡ ጠጪዎቹ በመገረም ራሳቸውን ነቀነቁ፡፡

አየርላንዳዊው በበኩሉ፣ ‹‹በኔ አገር አንድ ነገር የወሰደ ሰው ሁለት በነፃ ይጋበዛል›› በማለቱ ጠጪዎቹ ይበልጥ በመደነቅ
አጨበጨቡ፡፡

በመጨረሻ ስኮትላንዳዊው፣ ‹‹የናንተ መዝናኛ ሥፍራዎች ጥሩ ቢሆኑም እንደ ስኮትለንድ ሊሆኑ ግን አይችሉም፡፡ ስኮትላንድ ውስጥ አንድ መለኪያ በሒሳባችሁ ከጠጣችሁ፣
ሦስት በነፃ ትጋበዙና ባክብሮትና በፍቅር ቤታችሁ ድረስ ትሸኛላችሁ!›› አለ፡፡

እንግሊዛዊው በሸቀ፡፡ ‹‹አታጋን እባክህ፤ አሁን የተናገርከው አጋጥሞህ ያውቃል? በዓይንህ በብረቱ አይተሃል?›› በማለትም በቁጣ ጠየቀው፡፡

ስኮትላንዳዊው እየሳቀ፣ ‹‹እኔን ባያጋጥመኝም፤ እህቴን አጋጥሟታል›› አለው፡፡

-አረፈዓይኔ ሐጎስ ‹‹የስኮትላንዳውያን ቀልዶች (2005)


በድሮ ጊዜ ነው አሉ፡፡ ከብዙዎቹ ጦርነቶች በአንዱ ጊዜ፡፡ እንደተለመደው ሴቶች ለወታደሩ ሁሉ ቆሎ ቆልተው፣ አምሰው ያሳድራሉ፡፡

በማግስቱ ፤በዘመን ብዛት ቃልም ‹‹እንደሚባልግ›› ያልተረዳ አንዱ የዘመኑ ወታደር ጡሩምባውን ይዞ የሚከተለውን ለፈፈ፡፡

‹‹ጡ! ጡ! ጡ! ትላንትና የቆላችሁ፣ ያመሳችሁ ሴቶች ዛሬ ለሽክሸካ ትፈለጋላችሁ እና እንዳትቀሩ >>




እትዬ ትሁኔ ጉልት ሻጭ ባልቴት በመሞቻቸው ሰዓት እንዲህ ተናገሩ፡-

‹‹አባ እንግዲህ መሞቴ ነው፤ እንደሚያዩት እንኩዋን የሚወረስ የሚላስ የሚቀመስ ተቤት የለም! ያም ቢሆን ለሁለቱ ልጆቼ ምንም ሳላወርሳቸው አልሞትም፡፡ እዚህ
ከቤቴ በስተግራ ካለው ጎረቤቴ ጋር ያልቋጨሁት ጠብ አለኝ፣እሱን ልጆቼ እንዲጨርሱልኝ ተናዝዣለሁ››


ጊዜን በስላቅ

የሥዕል አስተማሪ ክፍል ውስጥ ይገቡና ለተማሪዎቻቸው የክፍል ሥራ ይሰጣሉ፡፡ መምህሩ ተማሪዎቻቸው ስለው እንዲያሳዩዋቸው የጠየቁት በሀዲዱ ላይ የሚጓዝ ባቡር ወይም ባቡሩን ከነሀዲዱ ቁጭ እንዲያደርጉላቸው ነው፡፡ ክፍለ ጊዜው
ከማለቁ በፊት እንዲታረምላችሁ በፍጥነት ሥሩ ይሉና ወደ መቀመጫቸው ያመራሉ፡፡ ቁጭ እንዳሉ እንቅልፍ ሸለብ ያደርጋቸውና ክፍለ ጊዜው ሊያልቅ 5 ደቂቃ ሲቀረው
ይነቃሉ፡፡ ወዲያውም ተማሪዎቻቸው የሠሩትን በየተራ እየተመለከቱ ሲያርሙላቸው ከተማሪዎቹ መካከል አንደኛው ሐዲዱን ብቻ ሥሎ ያሳያል፡፡ መምህሩ ሲመለከቱት ባቡሩ
የለም ሀዲዱን ብቻ ይመለከቱና ጥያቄ ያነሳሉ፡፡

መምህሩ፡-ስላችሁ አሳዩኝ ያልኳችሁ በሀዲድ ላይ የሚጓዝ ባቡር ነው፣ አንተ የሣልከው ደግሞ ሀዲዱን ብቻ ነው፤ ባቡሩስ ሲሉ
ይጠይቃሉ፡፡

ተማሪ፡- አይ ቲቸር እርስዎ እኮ እንቅልፍ ወስዶዎት እያለ ባቡሩ አልፏል፡፡ ለዚህ ነው ሀዲዱን ብቻ የሚመለከቱት


 ፍቅር በሒሳብ

በአንዳች ቅጽበት set ነትሽን አድንቄ ቀርቤ ላወራሽ ብፈልግ ስለፍቅርሽ እኔ ለፍቅር negative ነኝ ብለሽ ብታስደነግጭኝም እኔ ግን ለፍቅር positvie ሳስብም እኔ
radical ውስጥ የገባሁ ነኝ ብትይም ተማመንኩ፡፡ ከcomplex system ላስቀር negative ፍቅርሽን sub set ሆነሽብኝ ፍጹም ብታስቸግሪኝም በsine መስመር ወደ
አንቺ ብመጣ የአንቺ ምርጫ በcosine መስመር ሆኖ ቢያስከፋኝም ተስፋ ባለመቁረጥ በhorizontal line ወይስ
በsymptote ወደ አንቺ ለመቅረብ አንድ ሐሳብ መጣልኝ፤ ሳሰላስል ድንገት ወስኜ ለራሴ እንደ polynomila በ power በዝቼ rationalize ሆነ inverse ሆኜ በመምጣት እንዳለብኝ ወሰንኩ አንቺን ፈልጌ፡፡

የምር ግን አስቸጋሪ ነሽ ለፍቅር empty set ነሽ፡፡ በሂሳብ ቀመር በ subtracton ኧረ እባክሽ በmultiplication ደግሞም በaddition እኔ ልሆንልሽ የፍቅርሽ division:: የፍቅርሽ ውስብስብነት በlimit “x” goes to beta
አለመፈታቱ ቢሆንብኝ ስቃይ በሐሳብ ብዞር በቁጥሮች ጎራ በgraph ዎች መንደር በcircle አደባባይ በquadratic ሰፈር በcalculus እና በመደመር አንቺ ግን ክፋትሽ አሁንም undifined ነሽ፡፡ ግን solve ማድረጊያው የፍቅርሽ መንገዱ sequence አይደለም፤ አቤት ክፋቱ እኔ ግን ተስፋ
ባለመቁረጥ logarithm ተጠቅሜ exponentialን አብዝቼ በsolution set ቦታ ሆኜ perimeter ሽን አቅፌ vertical line ሽን አይቼ upper and lower
bounedሽን አረጋግጩ remainder ሽን በድካም አግኝቼ square root ሳላበዛ ተስፋ አደርጋለሁ እንደማግኝሽ፡፡ በfunction ቦታ ካልተገኘሽ የፍቅር slope ካልገባሽ የ
“x” “y” ዋጋ ካልሆንሽ የምር አሁንም ለፍቅር empty set ነሽ፤ ለፍቅር undefined ነሽ፤ ለፍቅር one over
zero ነሽ፤ ሁሌም ነሽ፡፡


  ሚስት ለበሏ እራት አቅርባ እየበላ እያለ “ጉዳችንን አልሰማህም” አለችው.

“ምን ተፈጠረ?”

“ልጅ”..

.“የምን ልጅ?”

“የ 15 አመት ልጃችን እኮ አረገዘች”

አሁንም ዝም ብሎ እየበላ “ከማን?” አለ...

“ከአለቃህ” ስትለው ፣ በድንገት
አባት ‘በስመአብ’ ብሎ የበላውን ‘ቱፍ’ ብሎ ይተፋል።

“ያናድዳል አይደል?” ስትለው...

“አይ ለሱ አይደለም ፣ ያልበሰለ
ድንች ልውጥ ነበር”


 ፹_ለውበትሽ አድናቆቴ ይህ ነው_(2)፹
........እድሜ የአፍሽ ዘበኞች ሆነው እንደሰራዊት ከፊት ለተሰለፉት ጥርሶችሽ፣ሊቃጠል የደረሰ አምፖል ለሚመስለው አይንሽ፣ጉንጭሽን መስሎ ከፊትሽ ለተለጠፈው አፍንጫሽ፣በዶማ እንደተፈነከተ ድንጋይ ለተተረከከው ሎሚ መሳይ ተረከዝሽ፣እንደጎሽ መውጊያ ለሚኮሰኩሰው ፀጉርሽ፣ምስጋና ይግባቸውና እነሆ ዛሬ የአለም ታላቋ አስቀያሚ አሰኝተውሻል።
........


  ቲቸር: "እስቲ በአዕምሮቹ ሳሉት: ውሃ ውስጥ ናችሁ: ዋና አትችሉም: ምን ታደርጋላችሁ?"

ቾንቤ እጁን አወጣ::

ቲቸር: "እሺ ቾንቤ!"

ቾንቤ "እኔ በአዕምሮዬ መሳሌን አቆማለሁ::"



 #ትንሹ ማሙሽ እድሜው ለትምህርት ሲደርስ አባቱ ትምህርት ቤት ይዞት ይሄድና ለተቀበለችው መምህርት እንዲህ የሚል መስጠንቀቂያ ይነግራታል::

" ይህ ልጅ ቁማር በጣም ነው የሚወደው:: እስከ ዛሬ እንዳየሁት የሚሸነፍ አይነት አይደለም:: ስለዚህ ምንም ነገር እናሲዝ ቢልሽ እሺ እንዳትይ ብሎ ይነግራታል::

አባት ገና እግሩ ከክፍሉ እንደወጣ ማሙሽ ቲቸሩን ጠርቶ "ቲቸር ከፊትሺ ፈገግታ ተነስቼ: ያረግሺውን ፓንት መገመት እችላለሁ::"

"እስቲ ገምት?" አለችው:: "ሃምሳ ብር አናሲዝ?" አላት:: ተስማምታ ከክላስ በሁላ ተቃጠሩ:: ክላሱ ሲያልቅ "እስቲ ግምትህ ምንድን ነው?" ማሙሽ "ነጭ!" አይደለም ብላ ቀሚሱአን ገልባ ስታሳየው ቀይ ነው::

"በቃ እሺ አባዬ ጋር አድርሽኝና ብሩን እሰጥሻለሁ::" አላት::

አባትየውን ገና ስታየው አስተማሪዋ "ዛሬ ማሙሽ አንድ ትምህርት ተማረ!"

አባት:- "ምን? "

አስተማሪ:- "መሸነፍን! ሃምሳ ብር አሸነፍኩት::"

አባት:- "በምን?"

አስተማሪዋ:-"ፓንትሽ ነጭ ነው ብሎ::"

አባት:- "እና ፓንትሽን አሳየሽው?"

አስተማሪዋ :- "አዎ!"

አባት:- "እናቱ አፈር የበላች! ከእኔ ጋር እኮ ክላሱ ከማለቁ በፊት ፓንቱአን አያለሁ ብሎ 100 ብር አሲዞኛል!"


 አንድ ሀብታም ሰው ፓርቲ አዘጋጅቶ ብዙ ሰው ጋበዘ:: በፓርቲው መሃል "አንድ ውድድር አለኝ" ብሎ አስታወቀ:: "ውድድሩ እዚህ የዋና ገንዳ ውስጥ አዞዎች አሉ:: በእነዚህ አዞዎች ውስጥ ዋኝቶ በህይወት የወጣ ሰው 3 ፍላጎቶችን ላሙዋላለት ቃል እገባለሁ::" አለ::

በመጀመሪያ ፍቃደኛ የሆነ ሰው ጠፋ:: በመኅል ግን የሆነ ሰው ዘሎ ገብቶ በፍጥነት መዋኛት ጀመረ:: ምንም አዞ ሳይነካው በህይወት ወጣ::

ባለሀብቱም ወደ ሰውዬው ጠጋ ብሎ "እንካን ደስ አለህ! ሶስቱ የምትፈልጋቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?"

ሰውዬውም ልብሱን እየጨማመቀ .... " ሽጉጥ : ጥይት እና የገፈተረኝን ሰው ማንነት!"::


 ስፍራው የአዕምሮ ህመም ችግር የለባቸው ሰዎች (ወይኔ እርዝመቱ - እብዶች ማለቴ ነው) ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ነው፡፡

በግቢው ውስጥ ያሉት እብዶች በጋራ ድምፅ "….13…..13….13…13…." እያሉ ይጮሃሉ፡፡ በዚህ ግዜ ወደ ስራው ለመሄድጫማውን እንኳን በደምብ ሳያስር ተጣድፎ ከቤቱ የወጣ አንዱ ወሬ ወዳድ ግለሰብ የፈለገው ሰዓት ይርፈድ እንጂ ይሄንንማ ምን እንደሆነ ማየት አለብኝ ብሎ ወደ ሆስፒታሉ ተጠግቶ ወደ ግቢው ውስጥ ለማየት የሚያስችለውን ቀዳዳ መፈለግ
ይጀምራል፡፡ ከትንሽ ፍለጋ በኋላ በበሩ ቁልፍ ስር ትንሽዬ ቀዳዳ አግኝቶ ወደ ውስጥ ለማየት አይኖቹን ሲያቁለጨልጭ ከውስጥ
ካሉት አንዱ እብድ በጣቱ አይኑን ይወጋዋል፡፡

ይሄን ግዜ ሌሎቹ ከኋላ "….14…..14….14 …14…." እያሉ መቁጠራቸውን
ቀጠሉ፡፡




አንድ አባት ልጃችውን ይዘው ሆስፒታል ይሄዳሉ:: ከዛምለዶክተሩ...

አባት : "ልጄ ቁልፍ ውጦአል ዶክተር::"

ዶክተር: "መቼ ነው የዋጠው?"

አባት: "ከ20 ቀን በፊት::"

ዶክተር: "እና ዛሬ ነው ይዘህ የምትመጣው?"

አባት: "ሌላ ቁልፍ ስለነበረን ነው:: ዛሬ እሱ ስለጠፋብኝ ነው::"


 በአንድ የኤርትራ ትምህርት ቤት ነው መምህሩ ተማሪወችን ይጠይቃል::

ከተማሪወች መሃል የፕሬዝዳንት ኢሳያስ ልጅ አለ እናም መምህር ጠየቀ"እስኪ ተማሪወች ከበራሪ እንስሳት መካከል ጥቀሱ "ይላል

ከተማሪወች መሃል እጁን ላወጣው የኢሳያስ ልጅ አንተ ሲባል "ዝሆን" ይላል አስተማሪውም አጨብጭቡለት ይላል፣ታላቅ ጭብጨባ በመሃል ጭብጨባውን የሰማ ረእስ መምህር ሲመጣ ምንድን ነው ሲል ጉዳዩ ይነገረዋል እናም ደግማችሁ አጨብጭቡለት ይልና ለመምህሩ"ወንድሜ እኛ ከምንበር ዝሆኑ ቢበር ይሻላል !!!!!አለው ይባላል!!


 የሳይንስ ክፍለ ጊዜ ነዉ መምህሩ 'ሰልፈሪክ አሲድ' ስለ ሚባለዉ የአሲድ አይነት በማስተማር ናቸዉ: :

''ልጆች አሁን ይህን የወርቅ እንክብል እዚህ አሲድ ዉስጥ ልከተዉ ነዉ እና አሲዱ ወርቁን የሚያበላሸዉ ወይም የማያበላሸዉ መሆኑን አስቀድሞ ሊነግረኝ የሚችል አለ"

"አያበላሸዉም ቲቸር" አለ አንዱ ልጅ ተሽቀዳድሞ

"ለምን"

"አሲዱ የሚያበላሸዉ ቢሆን ኖሮ እርሶ ቀዱሞዉኑ አሲዱ ዉስጥ አይከቱትማ" : :


 ለምን ደወልሽው ?
--------------- ---
አንድ ሴት ዉሀ ልትቀዳ ጎንበስ ስትል አንድ ጊዜ ያመልጣትና (Feswan) ድዉ ታደርገዋለች።

ዘወር ብላ ስታይ አለቃ ገብረሀና ከኋላዋ ቆመዋል። ከዛም ደንገጥ ብላ...

«አለቃ ለመሆኑ ሰአት ስንት ሆነ ስትላቸው?»

«አይ አንች ካላወቅሽዉ ለምን ደወልሽዉ?»
አሏት 


አንድ ልጁ ታስሮበት ብቻዉን የቀረ ገበሬ እስር ቤት ላለ ልጁ እንዲህ ሲል ፃፈ፦

“ዉድ ልጄ ፤ ይኸዉልህ አንተ በመታሰርህ ምክንያት በዚህ አመት እርሻ ቦታዉ ላይ ድንች ሳልዘራ ጊዜዉ ሊያልፍብኝ ነዉ፤ እኔ እንደሆንኩ ከእንግዲህ ደክሜያለሁ፤ምነዉ
በኖርክልኝ ኖሮ” አፍቃሪ አባትህ።

ከሳምንት በኋላ ገበሬዉ መልስ መጣለት፤

ምላሹም፡- “አባባ፤ የድንቹን መደብ እንዳትቆፍር፤ ሰወቹን የቀበርኳቸዉ
እዚያ ነዉ፡፡ ያንተዉ ልጅህ” ይላል፡፡

በሚቀጥለዉ ንጋት ላይ የፖሊስ መዓት መጥቶ የድንቹ ማሳ ላይ ፈሰሰ፤ የተቀበሩትን አስክሬኖች ለመፈለግ ሲቆፍሩ ቢዉሉም ምንም ሊያገኙ አልቻሉም ፡፡ ስለዚህ ገበሬዉን ይቅርታ ጠይቀዉ ሄዱ፡፡ ወዲያዉ ልጁ ለአባቱ እንዲህ የሚል
ሌላ ደብዳቤ ፃፈ፡-

“አባቴ፤ አሁን ድንችህን መዝራት ትችላህ፤ ካለሁበት ችግር አንፃር ላደርግልህ የምችለዉ ነገር ቢኖር ይሄ ብቻ ነዉ”


 ብልጥ ለብልጥ

እናት፡- ዮሐንስ እዚያ ኬክ ያስቀመጥኩበት መሳቢያ ውስጥ ጭራቅ መኖሩን አትርሳ፤ እሺ?

ዮሐንስ፡- እሺ እማምዬ አልረሳም፤ ግን ሁልጊዜ ኬክ ሲጠፋ ጭራቁን ለምን አትጠይቂውም? እኔን ብቻ ነው
የምትገርፊኝ ? 


 የፊደሏ ጣጣ

ጎልማሳው ለሥራ ጉዳይ ካለበት ብርዳማ የአሜሪካ ግዛት ወደ ሌላ ሞቃታማ ግዛት ይጓዛል፡፡ ባለቤቱም በቀጣዩ ቀን እንደምትመጣ ተነጋግረው ነበር፡፡

ጎልማሳውም ታዲያ የሆቴል ክፍሉ ውስጥ ሆኖ ለባለቤቱ የኢ-ሜይል መልዕክት ይልክላታል፡፡ ሆኖም ግን አድራሻዋን ሲጽፍ አንዲት ፊደል ይስትና የኢ-ሜይል መልዕክቱ ወደ ባለቤቱ መሄዱ ቀርቶ አቅጣጫውን ስቶ ወደ አንዲት ባለቸው ወደ ሞቱባቸው ባልቴት ዘንድ ይሄዳል፡፡

ሴትዬዋ የሃይማኖት ሰባኪ ባላቸው ከሞቱ ገና አንድ ቀናቸው ነበር፡፡
ሐዘን ላይ ያሉት ባልቴት የኢ-ሜይል መልዕክቶቻቸውን ሲፈትሹ (ቼክ ሲያደርጉ) ይህን መልዕክት ያዩና ይከፍቱታል፡፡

ወዲያው ግን ጮኸው መሬት ላይ ይዘረራሉ፡፡
ልጆቻቸውም ተሯሩጠው መጥተው ሲያዩ እናታቸው መሬት ላይ ወድቀዋል፡፡ በምን ምክንያት እንደሆነ ለማወቅ ወደ ኮምፒዩተሩ ተጠግተው ተመለከቱ፡፡

ኮምፒዩተሩ ስክሪን ላይ የተጻፈው መልዕክት:-

“ውድ ባለቤቴ እኔ ደርሻለሁ፡፡ ይገርምሻል፤ እዚህ በጣም ይሞቃል፡፡ ላንቺም ነገ መምጣት ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶ እየጠበቀሽ
ነው! ከልጆችሽ ተለይቶ መምጣቱ እንዳይከብድሽ ! ያንቺው!
የሚል ነበር፡፡

18 comments:

  1. wow bwtam des yilal

    ReplyDelete
  2. thank u that was good

    ReplyDelete
  3. በጣም ያዝናናል!

    ReplyDelete
  4. Very Essential; Thank you very much!

    ReplyDelete
  5. Nice, nice....ምርጥ ምርጥ ቀልዶች ናቸው! Please add?

    ReplyDelete
  6. heey its so funny!

    ReplyDelete
  7. ምርጥ ነው ቀጡሉበት

    ReplyDelete
  8. በጣም አሪፈፍ ነው በዚሁ ቀጥሉ

    ReplyDelete
  9. ተመችቶኛል ቀጥሉበት

    ReplyDelete
  10. ተመችቶኛል

    ReplyDelete
  11. አሪፍ ነው

    ReplyDelete

ጣዕም

Featured

ፍ ቅ ር