Sunday, May 22, 2022

ወንጀለኛው

ነገሩ እንዲህ ነው አንድ የታወቀ ወንጀለኛ በስንት መከራ ተያዘ። ተይዞ ፖሊስ መረመረው። በተያዘ በሳምንቱ በጠና ታሞ ሆስፒታል ይሄዳል። ታዲያ ዶክተሩ "ትርፍ አንጀት ስለሆነ ትርፍ አንጀቱ ተቆርጦ መውጣት አለበት" ብሎ ኦፕራሲዮን ተደርጎ ወጣለት። እንደገና በሳምንቱ ታመመ ዶክተሩ "ጉበቱ ግማሹ ስለተጎዳ ተቆርጦ መውጣት አለበት" ብሎ ኦፕራሲዮን ተደርጎ ወጣለት። እንደገና አሁንም በሳምንቱ ታመመና ሆስፒታል ሄደ። ዶክተሩ "አንዱ ኩላሊት ስራውን ስላቆመ መውጣት አለበት" ሲል ወንጀለኛውን ሲያመላልስ የነበረው ፖሊስ ወደ ዶክተሩ ጠጋ ብሎ እኔ ምልህ ዶክተር "ይህ ሰው ዘመድህ ነው እንዴ"? ይለዋል። ዶክተሩም "ኧረ ዘመዴ አይደለም። ምነው?" ሲለው ፖሊሱ ምን ቢል ጥሩ ነው?

"ቀስ በቀስ ከእስር ቤት እያወጣሀው እኮነው፡፡ እንደመኪና መለዋወጫ አካሉን ቀስ በቀስ እየከፋፈልክ ከእስር ቤት አስወጥተህ መልሰህ ልትገጣጥመው ይሆናላ"

Share:

ስኬት መንገድ ነው።

 "ለአንዳንድ ሰው ስኬት አግብቶ ልጅ መውለድ ሊሆን ይችላል፣ ለአንዳንድ ሰው ደግሞ ተምሮ ዲግሪውን መያዝ ሊሆን ይችላል፣ ለአንዳንዱ ደግሞ ደግሞ ሚሊዮን ብር ባንክ ማስቀመጥ ሊሆን ይችላል፣ ለእኔ ስኬቴ በየቀኑ ራሴን ማሸነፌ ነው፣ ወደ አልጋዬ ስሄድ ህሊናዬ ዛሬ ምን ሰርተሻል ብሎ ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ መስጠት ነው። በዛ ረገድ ደስተኛ ነሽ ወይ ከተባልኩ አዎ ስኬት ግን መንገድ ነው ብትሄጂበት ጥግ የለውም፣ ደግሞ ደስ የሚለው መንገዱ ነው።"

ሳያት ደምሴ


ተወዳጇ አርቲስት ሳያት ደምሴ

Share:

ሚስቴ ጠፋች 😂

 ሰውየው ፖሊስ ጣቢያ ደውሎ "ሚስቴ ጠፍታለች" ብሎ ያመለክታል።

#ፖሊስ፦ "ከጠፋች ምን ያህል ጊዜ ሆናት?"

#ባል ፦" አንድ ወር ሆኗታል"

#ፖሊስ ፦ "ለምን እስከዛሬ አላመለከትክም ?"

#ባል ፦ እስከ ትናንትና ድረስ መጥፋቷ ህልም ነበር የመሰለኝ። ከዛ ምንም የታጠበ ልብስ እንደሌለኝ ሳይ መጥፋቷን አመንኩ። 

Share:

ጣዕም

Featured

ፍ ቅ ር