አጫጭር ታሪኮች




የ12 ዓመቷ ታዳጊ ዘውትር በእጇ ቅጠላ ቅጠልና የተለያዩ ዕቃዎች ይዛ በዚህ መንገድ
ታልፋለች:: በአካባቢው ወዳለው የቀበና ወንዝ በመውረድ መጫወት ያስደስታታል:: እናቷ ግን አይለቋትም:: ቢሆንም እሳቸውን ተደብቃ መሔዷን አላቋረጠችም:: የአዕምሮ
ህመምተኛ ናት:: ይህቺን ልጅ አይቶ የማያዝንላት ሰው የለም:: ቀይ ቆንጆና የደስደስ ያላት ታዳጊ ናት:: የምታወራውን ነገር አታውቀውም:: እናቷ ዘውትር እያዩዎት ያለቅሱ የነበር ቢሆንም አሁን አሁን የሆነውን በፀጋ ከመቀበል ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው በመገንዘባቸው ዝምታን
መርጠዋል:: ብዙ ጸበል ሞክረው አልተሳካላቸውም::

ይቺን ህፃን የሚወዳት የዚህ ሰፈር ወጣት አለ ቀበና ሰፈር 24 ዓመቱ ነው:: ዘውትር
ከረሜላ ይገዛላታል:: እሷም ትወደዋለች:: ያጫውታታል:: ሣንቲም ይሠጣታል:: ብዙ
ጊዜ ከአይኑ እንድትጠፋ አይፈልግም:: አንድ
ቀን ከመንገድ ሲመለስ ወንዝ አካባቢ ጫወታ ላይ ሳለች ከረሜላ እንደሚገዛላት
ነግሮ ይዟት ወደ ቤቱ መጣ:: በዚህ ወቅት ግን የለመደችውን ከረሜላ አልገዛላትም:: የገባውን ቃል አላከበረም:: ይልቅስ መጥፎ
ድርጊት ተፈጠረ::

አልጋው ላይ ካስወጣት በኇላ ልብሶቿን አስወልቆ ደፈራት:: ክብረ ንፅህናዋ ተገሰሰ:: አሟታልና ጮኸች:: ከዚያን በኋላ ግን ከኪሱ ከረሜላ አውጥቶ ሲሰጣት ረሳችው:: ከቤቱ አውጥቶ ወደ ቤቷ ሰደዳት::

ከአንድ ሰዓት በኋላ ቤቱ በሀይል ተደበደበ:: ደነገጠ:: ወጣቶች ናቸው:: አንገቱን ይዘው አወጡት:: ፖሊስ ነበር:: ይዘውት ሄዱ:: የፈፀመውን ድርጊት አመነ:: ታዳጊዋ ቀሚሷ ላይ ደም ስለታየ እናቷ ምን እንደሆነች ጠይቀዋት ይህ ግለሠብ ያደረጋትን ነግራቸው ስለ ነበር ነው ለጎረቤት ሁኔታውን አሳውቀው ፖሊስ ጣቢያ የሄዱት:: ይህ ጨዋ መሳይ ወጣት ለፍትወቱ ጥማት ሲል ህፃን ለዚያውም የአዕምሮ ህመምተኛዋን በመድፈሩ : ይህም በራሱና በማስረጃ በመረጋገጡ ፍርድ ቤት የ12 ዓመት ፅኑ እስራት አከናንቦ ዘብጥያ ልኮታል:: ዕውን የአዕምሮ ህመምተኛው ከህፃኗና ከርሱ ማነው?

→ → አዲስ ጉዳይ መስከረም 2005 ዓ.ም


 የዘናጭ ልጅ ልቅሶ

እናቱ ለአሥራ አምስት ዓመት ልጇ የአክስቱን ሞት እንዴት እንደምትነግረው ተጨንቃለች፡፡ ይህቺ የአባቱ እኅት የሆነችው የልጁ አክስት ልጅ አልነበራትምና እንደ ልጇ ታየው ነበር፡፡ አብራው ኳስ ታያለች፤ አብራው ትዝናናለች፣ አብራው ታጠናለች፣ አብራው ትዋኛለች፣ አብራው ፊልም ታያለች፣ አብራው ኳስ ትጫወታለች፡፡
እንዲህ የምትሆንለትን አክስቱን ሞቷን ሲሰማ ያብዳል ብላ እናቱ ተጨንቃለች፡፡ እናም ትንቆራጠጣለች፡፡ ከትምህርት ቤት ሲመጣ መጀመርያ መክሰስ አበላችውና ወደ መኝታ ቤት ወሰደችው፡፡ ከዚያም በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ መኖርና መሞት ያለ መሆኑን፤ አንዳንድ ጊዜ የምንወዳቸው ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉ ትነግረው ጀመር፡፡ ልጁ ግራ ገባው፡፡
‹እይውልህ ልጄ› አለች እናቱ ድምጽዋ ሆድዋ ውስጥ ገብቶ ሊጠፋ እየደረሰ፡፡ ‹‹ያች የምትወድህና የምትወዳት አክስትህ በድንገት ትናንት ማታ ዐረፈች›› አለችው፡፡
‹‹ምን?›› አለና ሶፋው ላይ ተደፍቶ ድምጽ ሳያወጣ አለቀሰ፡፡ ከዚያም ከተደፋበት ተቃንቶ አንገቱን ሰበረና ይነቀንቅ ጀመር፡፡
እናቱ የሚያደርገውን ሁሉ እንዲሁ ትከታተላለች፡፡ እንደሰማ አገር ይያዝልኝ ይላል፤ በድንጋጤ አቅሉን ይስታል፤ መሬት ላይ ይፈጠፈጣል፤ ዓባይ ዓባዩን ያነባዋል ብላ ነበር የጠበቀችው፡፡ እንዲህ ቢሆንባት ምን ማድረግ እንደምትችል ነበር ስትጨነቅ የቆየችው፡፡ አንዳንድ ጎረቤቶቿንም ስትጠራቸው መጥተው እንዲረዷት ተማጽናቸው ነበር፡፡
ሁሉም ግን እንዳሰበችው አልሆነም፡፡
‹‹አንተ፣ ያች እንደዚያ የምታሞላቅቅህ አክስትህ ሞታ እንዲህ ነው የምትሆነው›› አለችው ተናድዳ፡፡
‹‹ምን ሆንኩ?››
‹‹አታለቅስም እንዴ?››
‹‹እያለቀስኩ አይደል እንዴ፤ ዕንባዬን አታይውም››
‹‹ለእርሷ እንደዚህ ነው የምታለቅስላት፤ ማፈሪያ ነህ፡፡ እርሷኮ ላንተ ያልሆነችው የለም፡፡ እንደ ሕጻን አብራህ ትጫወታለች፤ እንደ ጓደኛ ፊልም ቤት ይዛህ ትገባለች፤ እንደ እናት ትሳሳልሃለች፤ ለእርሷ እንደዚህ ነው የምታለቅሰው›› እናቱ አዝና ሶፋው ላይ ዘርፈጥ ብላ ተቀመጠች፡፡
‹‹ታድያ እንዴት ነው ለርሷ የሚለቀሰው?›› አላት ዕንባውን እየጠረገ፡፡
‹‹እትዬ እትዬ፤ ጉድ አደረግሽኝ፤ ሳትነግሪኝ፤ ምነው ጥለሽኝ ሄድሽ፤ እየተባለ ነዋ››
‹‹እንዴ እማዬ እንዴት ልትነግረኝ ትችላለች? በድንገት ነው የሞተችው አላልሽኝም? ደግሞስ ጥለሽኝ ሄድሽ ማለት ምን ማለት ነው? እና ይዛኝ እንድትሄድ ፈለግሽ?››
እናቱ አፏን እጇ ላይ ጭናለች፡፡
‹‹አይ የዛሬ ዘመን ልጆች፤ የልቅሶው ወግ እንደዚህ ነው፤ የቅርብ ዘመድ እንዲህ ነው የሚያለቅሰው፤ የሸንኮሬ ልጅ ‹ጥሪኝ አክስቴ ጥሪኝ› እያለ ጠዋት ሲያለቅስ ባየኸው››
‹‹እንዴ እርሱ ደግሞ ምን ነክቶታል፡፡ ባለፈው ‹ና ግቢውን እናጽዳ› ብላ ስትጠራው ያልመጣውን አሁን የት ነው ጥሪኝ የሚላት? ውሸታም ነው፡፡ አሁን አንቺ ብትጠራሽ ትሄጃለሽ?››
እናቱ አማተበች፡፡ ‹‹ደረቅ ነህ ልጄ፤ ደረቅ ነህ፤ ነውር ነው፣ በእውነት ነውር ነው እንደዚህ አይባልም፡፡ በዚህ ዓይነት ለእኔም ጊዜ እንደዚሁ ነው›› ከልቧ አዘነች፡፡ ደግሞም ታያት፡፡ እርሷ ሞታ፤ ልጇ ዝም ሲል፤ ሰው ሁሉ ዓይንህን ላፈር ሲለው፡፡ ‹አሁን የርሷ ልጅ ይኼ ይሁን› እያለ በዓይኑ አፈር ድሜ ሲያበላው፡፡ ታያት፡፡
‹‹እማዬ ግን አንቺ የምትፈልጊው ካሰብሽው ቦታ የሚደርስልሽ ልጅ ነው ወይስ ስትሞቺ የሚያለቅስልሽ? እኔን ሠራ ነው ወይስ እንዳለቅስ? ደግሞም ያኔ የምሆነውን ያኔ ነው ማወቅ የሚቻለው፡፡ እኔ ማዘን ያለብኝ ለራሴ ነው ወይስ ለሰው? ኀዘን እንደ ፊልምና ድራማ ለሕዝብ መታየት አለበት?››
‹‹እርሱማ ልክ ነበርክ ልጄ፤ ግን ሰው ይቀየምሃል፤ ዘመዶቻችን ይቀየሙሃል፡፡ በልቶ ካጅ፣ ወጭት ሰባሪ፣ እጅ ነካሽ ይሉሃል ልጄ፡፡››
‹‹ይበሉኛ፤ እኔ የት እሰማቸዋለሁ››
‹‹እኔ እሰማለኋ››
‹‹አትስሚያቸዋ፤ ተያቸው››
‹‹እንዴት አድርጌ ልጄ፡፡ የሰው ምላስ መርዝ ነው ይገድላል፡፡ ዱላ ነው ይሰብራል፡፡ እኔ ልጄን በክፉ እንዲያነሡብኝ አልፈልግም፡፡ የሰው ጥርስ ውስጥ ትገባለህ ልጄ፡፡ ደግሞ እርሷ ናት እንዲህ ያደረገችው ይሉኛል፡፡ የአባትህ ዘመዶች ይጠምዱኛል፡፡ አንተስ ብትሆን አክስትህ ናት፤ እንዲያ የምትወድህ አክስትህ ናት፤ ምናለ ብታለቅስላት?››
‹‹ቆይ ግን አሁን ማልቀስ ያለብኝ ለእርሷ ነው ለእኔ››
‹‹እንዴት እንዴት?››
‹‹አጉራሼ፤ አልባሼ፤ ጠያቂዬ፤ ሆዴ፤ ደጋፊዬ እያሉ የሚያለቅሱት ለሟቹ አዝነው ነው ወይስ እነርሱ ስለቀረባቸው? ማረፊያችን ነበርሽ፤ ማን ላመትባል ይጠራናል ብሎ ማልቀስ አሁን ለሟች ነው ለራስ? ቆይ ግን ሰው ስለ ሰው የሚመሰክረው ሲሞት በልቅሶ ዜማ ብቻ ነው እንዴ?››
‹‹የዛሬ ልጆች መፈላሰም ትወዳላችሁ እንዴው፤ አለቀሰ አላለቀሰም? የሚል እንጂ ለምን አለቀሰ? የሚል ዕድር እስካሁን የለም፡፡ አቤት እገሌ እንዴት ቢወዳት ነው፤ አቤት እገሌ አለቃቀሱን ስትችልበት ይባላል እንጂ ለራሱ ነው ወይስ ለሟች? ተብሎ ድንኳን ውስጥ አይጠየቅም፡፡ ይኼው በቀደም አንዱ የነ እትዬ የሰው ሐረግ ድንኳን ገብቶ ለያዥ ለገራዥ እስኪያስቸግር መሬት እየወደቀ ሲያለቅስ ቆየ፡፡ ሰው ሁሉ ምን ቢዋደዱ ነው እስኪል ድረስ፡፡ ማን ይገላግለው፡፡ ሰውን ሁሉ ዕንባ በዕንባ አራጨው፡፡ በመጨረሻ በቄስ ተገዝቶ አቆመና ቀና ሲል ሰዎቹንም አያውቃቸውም፤ ፎቶዋን አያውቀውም፡፡ ለካስ ድንኳን ተሳስቶ ኖሯል፡፡ ይቅርታ ጠይቆ ወጣ አሉ፡፡ እዚያኛውም ሄዶ እንዲሁ ሲያለቅስ ነበረ አሉ፡፡››
‹‹እና አሁን ይኼ በማያገባውና በማያውቀው ልቅሶ ገብቶ የሚያለቅሰው የፍቅር መግለጫ ነው?››
‹‹ባህሉ ነዋ ልጄ፡፡ መቼም ቢሳሳትም ልቅሶውን ሁላችንም አደነቅንለት፡፡ ወንድ ልጅ እንደዚህ ሲያለቅስ እኔ አይቼ አላውቅም፡፡ ‹ዘመዶቹ ታድለው› ነው ያልነው፡፡ አስለቃሽም አያስፈልጋቸው፡፡ እኛን እንኳን የረሳነውን ሁሉ እያስታወሰ አስለቀሰንኮ፡፡››
‹‹እሺ አሁን ምን አድርግ ነው የምትይኝ››
‹‹እንሂድና አንድ ጊዜ ብቻ ሰው እንዲያይህ ‹አጉራሼ አልባሼ› ብለህ ጯጩኸኽ እንገላገል››
‹‹እኔንኮ አላጎረሰችኝም፣ አላለበሰችኝም››
‹‹ይኼ ልጅ ምን ሆኗል ዛሬ፡፡ አብራህ አልነበረም ኳስ የምታየው? ከርሷ ጋር አልነበረም ፊልም የምትገባው? ደውለህ ለርሷ አልነበረም እገሌ አገባ፤ እገሌ ተሸነፈ ትላት የነበረው? ሶደሬ አልወሰደችህም? ጌም አልጋበዘችህም? ዋና አላስዋኘችህም? በጣም ታሳዝናለህ፡፡ እንዴት እንደዚህ ትላለህ?›› ተቀየመችው፡፡
‹‹እና ይኼ ማጉረስ ማልበስ ነው? የምጎርሰው ራሴ ነኝ፣ የምለብሰውም ራሴ ነኝ›› አላት፡፡
‹‹ኤዲያ፤ የስምንተኛው ሺ ልጆች፤ አባባሉንም አታውቁትም፡፡ ይህኮ አባባል ነው፡፡በል አሁን ከሄድክ እንሂድ ሰው ጥርስ ውስጥ እንዳታስገባኝ፡፡ ››
‹‹እኔኮ አልችልበትም፡፡ እንደናንተ ማድረግ አልችልበትም፡፡ እናንተኮ የብዙ ዓመት ልምድ አላችሁ››
‹‹ሆሆይ›› ሳቋ መጣ ‹‹የመሥሪያ ቤት ቅጥር አደረግከው እንዴ ልምድ ምናምን የምትለው፡፡ ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም ሲባል አልሰማህም፡፡››
‹‹እሺ ሄጄ ምን ላድርግ?››
‹‹ድንኳን እስክንደርስ ዝም ትላለህ፡፡ ልክ ድንኳኑ አካባቢ ስንደርስ እኔ እጮኻለሁ፣ አንተም እኔን ተከትለህ ትጮህና ‹አልሰማሁም ነበር፤ አልሰማሁም ነበር› እያልክ ኡኡ ትላለህ››
‹‹እንዴ እማዬ ይኼው ሰማሁ አይደል እንዴ፤ ይኼማ ውሸት ነው፡፡››
‹‹ልጄ እኔ እናትህን ስማኝ፤ እንደዚያ ነው የሚባለው፡፡ አባባል ነው፡፡ ደግሞ በገላጋይ ካልሆነ በቀር ልቅሶህን እንዳታቆም››
‹‹እንዴ ዝም በል እያሉኝ ልቀጥል? እንዲያውም ምክንያት ካገኘሁ ተገላገልኩ››
‹‹እንዲያውም ከቻልክ መሬት ውደቅ››
‹‹እንዴ እማዬ እኔ በረኛ አይደለሁ ለምን መሬት እወድቃለሁ››
‹‹በርህ ይጥፋና ባህል ነው አልኩህ፡፡ ሰው ያደንቅሃል፤ እንዲያውም ትንሽ ተንከባለል››
‹‹እማዬ አሁንስ አበዛሽው፣ ሳቄ ቢመጣስ፡፡ አንቺኮ የድራማ አክት የምታስጠኚኝ ነው የመሰልሽኝ››
‹‹በል ተወው ደግሞ ታዋርደኛለህ›› አለችና ወደ ምኝታ ቤት ገብታ ጋቢና ፎጣ ይዛ መጣች፡፡
‹‹በል እንካ ጋቢውን ትከሻህ ላይ፣ ፎጣውን አንገትህ ላይ አድርግ፡፡ ስታለቅስ በፎጣው ተሸፈን፡፡ ዕንባ እንኳን ባይመጣብህ የሚያይህ የለም፡፡››
‹‹የልቅሶ ቤት ዩኒፎርም መሆኑ ነው›› አላት፡፡ ‹‹ሆሆ›› አለች አንገቷን እየነቀነቀች፡፡
ሄዱ፡፡ ልቅሶው ቤት በር ላይ ከመድረሳቸው በፊት አንድ ጓደኛው ደወለና የሆነ የእግር ኳስ ውጤት ነገረው፡፡ ውጤቱ አስደሳች ነበር፡፡ እርሱን እያሰበ ድንኳኑ በር ላይ ሲደርሱ እናቱ ያስጠናችው ነገር ተረሳው፡፡ ጉዱ ፈላ፡፡ መኪናዋን ሲያዩ ለቀስተኞቹ ተንጋግተው ከድንኳኑ ወጡና ከበቧቸው፡፡ እናት ከመኪናዋ እየጮኸች ወረደች፡፡ ልጁ ግን የሚባለው ነገር ጠፍቶታል፡፡ ከእናቱ ጎን ሆነና በፎጣው ተሸፍኖ ‹‹እማዬ ምን ነበር ያልሽኝ፤ ስቴፑ ጠፋኝኮ›› አላት፡፡ እናቱ በዓይነ መዓት አየችውና ጩኸቷን ቀጠለች፡፡
እርሱ ግን በአፉ እየጮኸ በልቡ ስቴፑን አሰበው፡፡ አልመጣለት አለ፡፡ ቀና ሲል የአክስቱን ፎቶ በአንድ አልቃሽ እጅ ላይ አየው፡፡ ያን ጊዜ የሆነ የኀዘን ስሜት መጣበት፡፡ ልቡ ተንቦጨቦጨ፡፡ ትዝ አለው ነገር ዓለሙ፡፡ እናም ወደራሱ ልቅሶ ተመለሰ፡፡
‹‹እትዬ እትዬ አይስክሬም ማን ይገዛልኛል፤ ሶደሬ ማን ይወስደኛል፤ ጌም ማን ያጫውተኛል፤ እትዬ እትዬ ኳስ ከማን ጋር አያለሁ፡፡ ሩኒ ሲያገባ ለማን እነግራለሁ፤ ሮናልዶ ሲስት ከማን ጋር አወራለሁ፤ ሜሲ ሲያገባ ለማን እደውላለሁ፡፡ እትዬ ደውይልኝ፤ ማን አገባ በይኝ፤ ማን ተጫወተ በይኝ፤ እትዬ፡፡ እትዬ ዛሬኮ ማንቼ ይጫወታል፤ ከማን ጋር አያለሁ፡፡ እትዬ የዛሬው ጨዋታኮ ወሳኝ ነው›› አስነካው፡፡
ወዲያው አንድ በእርሱ እድሜ ያለ ልጅ ነጠር ነጠር እያለ መጣና በጆሮው ‹‹ማንቼ ተጫውቶ ቅድም ተሸነፈኮ›› አለው፡፡
ይህን ጊዜ መሬት ላይ ወድቆ እየተንከባለለ ‹‹እርምሽን ባትኖሪ ማንቼ ተሸነፈልሽ፤ እርምሽን ባትኖሪ ቫምፐርሲ ሳያገባ ቀረ፡፡ እርምሽን ባትኖሪ ማንቼ ነጥብ ጣለ፡፡ የፈራሁት ይኼን ነበር፡፡›› ለቀስተኛው ሁሉ ልቅሶውን ቀስ በቀስ እየተወ እርሱን ያየው ጀመር፡፡ እናቱ ግን ሾልካ የት እንደገባች አልታወቀም፡፡ 



ልብ የሚነካ ታሪክ ያንብቡትና አስተያየት ይስጡ
***
እናቴ አንድ እይን ብቻ ነው ያላት በዛም የመጣ
በጣም እጠላታለው::አባቴ...አ ባቴ ደሞ የአራስ
ቤት ልጅ እያለው ነው የሞተው እሱ ከሞተ በኋላ
እኔና እናቴ በደሳሳ ጎጆዋችን ከድህነትጋ መኖር
ጀመርን::አባዬ ያስቀመጠው ገንዘብ ሲያልቅ
እናቴ በራችንጋ ትንሽዬ ሱቅ ከፍታ
መስራትጀመረች እማ ለኔ የማታደርግልኝ ነገር
የለም እኔ ግን በሷ አፍር ነበር ትዝ ይለኛል 5ኛ
ክፍል የወላጆች ቀን እናቴ ትምህርት ቤት አበባ
ይዛልኝ መጣች "እንዴት እንዲ ታደርገኛለች?
ማን ነይልኝ አላት?" ተሸማቀኩ በጥላቻ አይን
ገልምጫት እየሮጥኩ አዳራሹን ለቅቄ ወጣው::
በሚቀጥለው ቀን ት/ቤት ስመጣ ጓደኞቼ"እናቱ
1 አይን ነው ያላት"እያሉ ሲያወሩ ሰማዋቸው
በውስጤ ምናለ እናቴ ከዚች አለም ብጠፋ ብዬ
ተመኘው እቤት ስደርስም "ደስይበልሽ በጓደኞቼ
አሳቅሽብኝ....ቆይ እንድ አይንሽ የት ሄዶነው?
ሁሌ እንዲ ከምታሸማቂኝ ለምን አትሞቺም?"
ብዬ ጮህኩባት ምንም መልስ ሳትሰጠኝ
ወጣች::እንዲ ማለቴ ስሜቴን ቢኮረኩረኝም
ለረጅም ጊዜ ልላት ያሰብኩትን በማለቴውስጤን
ቀለል አለኝ
ብዙም ስሜትዋን የጎዳሁት አልመሰለኝምነበር
ያን ቀን ማታ ከእንቅሌፌ ተነስቼ ውሃ ልጠጣ
እቃ ቤትስገባ እናቴ እኔን ላለመቀስቀስ ቅስ ብላ
ስታለቅስ አገኘዋት ቅድም ባልኳት ነገር
እንደሆነ ገባኝ::
አሳዘነችኝ!
ድምፄን ሰምታ ቀና ስትል ካንዱ
አይንዋየሚወርዱ እንባዎቿን እየዋቸው::አይንዋ
በእንባ ተሞልቶ ሳየውይበልጥኑ ጠላኋት! በዛው
ቅፅበት ለራሴ እንድ ነገር ቃል ገባው አድጌ
ስኬታማ ስሆን እንድ አይናማዋን እናቴን ጥያት
እንደምሄድ!
ከዛን ቀን ጀምሮ ጠንክሬ መማር ጀመርኩ
እናቴን ትቻት ወደ ከተማ በመሄድ አለ በሚባል
ዩንቨርስቲ ውስጥ ስኮላርሺፕ አግኝቼ በነፃ
ትምህርቴን ተከታትዬ ጨረስኩ ጥሩ ስራ
ያዝኩ፤የራሴን ቪላ ገዛው ሚስት
አግብቼምልጆች ወለድኩ::አሁን የተመኘሁትን
የልጅነት ህይወት እየኖርኩ እገኛለው::በጣም
ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ገንዘብ አለኝ፤ቆንጆ ቤት
አለኝ፤ደስተኛ ቤተሰብ አለኝ ከሁሉም በላይ ግን
የምጠላትን እናቴን የማላገኝበት ሩቅ ቦታ
ነውናየምኖረው ደስተኛ ነኝ:: አንድ ቀን ግን
ያላሰብኩት ዱብ እዳ መጣብኝ "ምን?!
ማነው ?!" እናቴ ነበረች ፀጉሮችዋ ሸብተው
ከስታና የተቀዳደዱ ቆሻሻ ልብሶች ለብሳ መጣች
ላምን አልቻልኩም ቤቴን እንዴት አወቀችው?!
ህፃንዋ ልጄ ፈርታት ሮጣ ወደቤት ገባች
እንዳላወቀ በመምሰል "ሴትዮ ምን ፈልገሽ
ነው?
የሰው ቤት ዝም ተብሎ እይገባም እሺ ውጪልኝ
ከቤቴ!!"አልኳት ኮስተር ብዬ እናቴ ደነገጠች "
ይቅርታ ጌታዬ አድራሻ ተሳስቼ ነው" ብላኝ
ወጣች.....ተመስገን አላወቀችኝም::ይህ ከሆን
ካንድ ወር በኋላ ለድሮ ት/ቤቴ የመዋጮ
ፕሮግራም ተዘጋጅቶ የት/ ቤቱ ዳይሬክተር
ደውለው ጠሩኝና ሄድኩ ፕሮግራሙ ሲያልቅ
በዛውም ያደኩበት ቤት ምን እንደሚመስል
ለማየት ስሄድ እናቴ መሬት ላይ ተዘርራ
አገኘዋት::ሞታለች!! ምንም
አላላቀስኩም::እጇ ላይ ወረቀትአየውና አንስቼ
ማንበብ ጀመርኩ
ለኔ የፃፈችው ደብዳቤ ነበር...እንዲህ ይላል "ውድ
ልጄ,ካሁን በኋላ ሕይወት ማለትለኔ ምንም
አይደለችም::እንተ ወደምትኖርበት ከተማም
ተመልሼ አልመጣም::ልጄ ከምንም በላይ ግን
ናፍቆትህ ሊገድለኝ ነው ለምን አንድ አይን ብቻ
እንዳለኝ ጠይቀከኝ አልነገርኩክም ነበር
እውነታው ይህ ነው ልጄ.....ልጅ እያለክ ከባድ
የመኪና አደጋ ይደርስብክና አንድ አይንክ ይጠፋል
እንደማንኛውም እናት ያለ አንድ አይን ስታድግ
ማየት አልችልምና የኔን አይን አውጥተው ላንት
እንዲያረጉልህ ዶክተሮቹን ጠይቄ ፈቃደኛ ሆነው
አደረጉልህ.....
ለዚ ነው እንድ አይናማ የሆንኩብክ::እይዞህ ልጄ
ባደረካቸው ነገሮች ተቀይሜህ አላውቅም ነበር
ባለፈው እቤትክ መጥቼ የልጄን ልጅ በማየቴ
በጣም ተደስቻለው::ለወደፊትም በደስታ
እንደምትኖርም ተስፋ አደርጋለው::ልጄ እናትህ
በጣም ትወድሃለች"
.....አንብቤ ስጨርስ በሁለት እግሮቼ መቆም
አቃተኝ.እማ.....እማ........እማ እንባዬን እየዘራው
ምስኪኗን እናቴን አቅፌ ተንሰቀሰኩ ለኔ ብላ
ህይወትዋን የሰጠችውን እናቴን በራሴ እጅ
ገደልኳት...
ሞራል: እናት ማለት እውነተኛ ፍቅር ናት::
ክብር ይገባታል የሷን ብድር በምድር ላይ ማንም
በምንም ሊከፍለው አይችልምና ከመሞቷ በፊት
የሚገባትን ክብር እንስጣት::
እስታውስ:ሁላችንም አንድ እናት ነው ያለችን::

7 comments:

ጣዕም

Featured

ፍ ቅ ር