Friday, October 14, 2016

ወይ ፍቅር...!

አንድ ወጣት ፍቅረኛውን ሞተር ሳይክሉ ላይአፈናጦ በሰአት160 ኪሎ ሜትር ይከንፋል።
ልጅት፦ እባክህ ፍጥነት ቀንስ የኔ ፍቅር ፈራሁ እኮ ልጅ፦ እንድንዝናና ብዬ ነው
ልጅት፦ ኖ ፍቅር በጣም አስፈሪ ነው፤ ፕሊስ
ፍጥነት ቀንስ
ልጅ፦ እሺ እንድቀንስልሽ እንደምትወጂኝ ንገሪኝ
ልጅት፦ አፈቅርሀለሁ የኔ ቆንጆ። እሺ አሁን ቀንሰዋ
ፍቅር ልጅ፦ ሳም አድርጊኝና
ልጅት፦ ወገቡን እንቅ አርጋ እንደያዘች ሳምምምም አደረገችው
ልጅ፦ በጣም ስለሞቀኝ ሄልሜቴ ደሞ አንሺልኝና አንቺ አጥልቂው አላት። እንዳላት አደረገች።
በማግስቱ አንድ የአገሬው ጋዜጣ እንዲህ የሚል ዜና ይዞ ወጣ 
''አንድ ሞተር ሳይክል በፍሬን ብልሽት ምክንያት ተጋጭቶ ሞተሩን ሲያሽከረክር በነበረው ወጣት ላይ የሞት አደጋ ሲከሰት አብራው
የነበረች ፍቅረኛው ግን ተርፋለች።
ለካ...
ሞተሩን ያሽከረክር የነበረው ፍቅረኛዋ ድንገት ፍሬን እንደተበላሸበት ሲገባው እሷ እንዳታውቅ በማድረግ የመጨረሻ የፍቅር ቃሏን ተቀብሎ፣ የስንብት በከንፈሯ ተስሞ፣ ሄልሜቱን እሷ እንድታጠልቅ አድግርጎ፣ እሷ በህይወት
እንድትኖር ራሱን ለመስዋዕትነት እያዘጋጀ ነበር !!! እንደዚ አይነት ፍቅር ይስጠን!!!

Share:

Wednesday, October 12, 2016

ካነበብኩት ላካፍላችሁ


-ፍቅር የሚጠይቀው ብቸኛ ስጦታ "ፍቅር" ነው።
-ቅናትን እንደ ሣቅ የሚያስፈራው የለም።
-ያየውን ሁሉ ለመያዝ የሚጥር አንድ ቀን እባብ

ጨብጦ ይነደፍል።

-በአለም ላይ ከፍተኛ መራራ ነገር ቢኖር ራዕይ ማጣት ነው።
-በኢላማህ የማትተማመን ከሆነ ወደ ነብር አተኩስ።
-ብርቱካን መጨመቁን ቢያቅ ውሀ አይዝልም ነበር።
-ለማመን እንጅ ላለማመን ምክኒያት አያስፈልግም።
-በፍቅር የተነሳ ልብ በፍቅር ይሰክናል
-ቅናትን የሚፈጥረው ፍቅር ሣይሆን እራሥ ወዳድነት ነው።
-መሣሣት ሰባዊነት ሲሆን ስህተትን ማመን ጻድቅነት
ነው።
-ማለዳ ስንነሳ ልብ እንበል ከሀብት ሁሉ የሚልቅ 24
ሰዐት የኛ ነው።
-ባልና ሚስት በጋራ የሚተነፍሥ ሣንባ ባይኖራቸውም በጋራ የሚጓዝ
ሰንሰለት አላቸው።
- ሰው ጥፋቱን ሲያምን ይከበራል እንጅ
አይዋረድም።
Share:

Tuesday, October 11, 2016

ፍቅር_ማለት_????


_ፍቅር ማለት ዉበትን ፍለጋ አይደለም፣
_ፍቅር ማለት ጥቅምን ፍለጋ አይደለም፣
_ፍቅር ማለት ዝሙትን ፍለጋ አይደለም፣

_ፍቅር ማለት በደስታ ጊዜ መተቃቀፍ አይደለም፣
_ፍቅር ማለት ስለተወደዳችሁ መዉደድ አይደለም፣
#ፍቅር_ማለት ከማንነት የፀዳ
#ፍቅር ከማዳላት የራቀ
#ፍቅር ከመፍረድ እጁን ያወጣ
በመከራም በሀዘንም በደስታም መተሳሰብ መረዳዳት እናንተ ያላገኛችሁትን ነገር ለሌሎች መመኘት ፤ጠላትህን መዉደድ ፣ በናንተ እንዲፈፀም የማትፈልጉትን በሌላ ሠዉ አለመፈፀም፣ ነገ ተመልሶ በራሳችን መፈፀም አይቀርምና፣
#ፍቅር_ማለት_ይኸ_ነዉ_ለመስዋት የማይሠሥት ፍቅር መስዋትን ድል የሚያደርግ ፍቅር ይኑር በቤታችሁ!!!!
Share:

ጣዕም

Featured

ፍ ቅ ር