Sunday, May 22, 2022

ወንጀለኛው

ነገሩ እንዲህ ነው አንድ የታወቀ ወንጀለኛ በስንት መከራ ተያዘ። ተይዞ ፖሊስ መረመረው። በተያዘ በሳምንቱ በጠና ታሞ ሆስፒታል ይሄዳል። ታዲያ ዶክተሩ "ትርፍ አንጀት ስለሆነ ትርፍ አንጀቱ ተቆርጦ መውጣት አለበት" ብሎ ኦፕራሲዮን ተደርጎ ወጣለት። እንደገና በሳምንቱ ታመመ ዶክተሩ "ጉበቱ ግማሹ ስለተጎዳ ተቆርጦ መውጣት አለበት" ብሎ ኦፕራሲዮን ተደርጎ ወጣለት። እንደገና አሁንም በሳምንቱ ታመመና ሆስፒታል ሄደ። ዶክተሩ "አንዱ ኩላሊት ስራውን ስላቆመ መውጣት አለበት" ሲል ወንጀለኛውን ሲያመላልስ የነበረው ፖሊስ ወደ ዶክተሩ ጠጋ ብሎ እኔ ምልህ ዶክተር "ይህ ሰው ዘመድህ ነው እንዴ"? ይለዋል። ዶክተሩም "ኧረ ዘመዴ አይደለም። ምነው?" ሲለው ፖሊሱ ምን ቢል ጥሩ ነው?

"ቀስ በቀስ ከእስር ቤት እያወጣሀው እኮነው፡፡ እንደመኪና መለዋወጫ አካሉን ቀስ በቀስ እየከፋፈልክ ከእስር ቤት አስወጥተህ መልሰህ ልትገጣጥመው ይሆናላ"

Share:

ስኬት መንገድ ነው።

 "ለአንዳንድ ሰው ስኬት አግብቶ ልጅ መውለድ ሊሆን ይችላል፣ ለአንዳንድ ሰው ደግሞ ተምሮ ዲግሪውን መያዝ ሊሆን ይችላል፣ ለአንዳንዱ ደግሞ ደግሞ ሚሊዮን ብር ባንክ ማስቀመጥ ሊሆን ይችላል፣ ለእኔ ስኬቴ በየቀኑ ራሴን ማሸነፌ ነው፣ ወደ አልጋዬ ስሄድ ህሊናዬ ዛሬ ምን ሰርተሻል ብሎ ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ መስጠት ነው። በዛ ረገድ ደስተኛ ነሽ ወይ ከተባልኩ አዎ ስኬት ግን መንገድ ነው ብትሄጂበት ጥግ የለውም፣ ደግሞ ደስ የሚለው መንገዱ ነው።"

ሳያት ደምሴ


ተወዳጇ አርቲስት ሳያት ደምሴ

Share:

ሚስቴ ጠፋች 😂

 ሰውየው ፖሊስ ጣቢያ ደውሎ "ሚስቴ ጠፍታለች" ብሎ ያመለክታል።

#ፖሊስ፦ "ከጠፋች ምን ያህል ጊዜ ሆናት?"

#ባል ፦" አንድ ወር ሆኗታል"

#ፖሊስ ፦ "ለምን እስከዛሬ አላመለከትክም ?"

#ባል ፦ እስከ ትናንትና ድረስ መጥፋቷ ህልም ነበር የመሰለኝ። ከዛ ምንም የታጠበ ልብስ እንደሌለኝ ሳይ መጥፋቷን አመንኩ። 

Share:

Monday, March 13, 2017

ለተማሪዎች፣ሰራተኞችና ሌሎች በጣም ጠቃሚ አንድሮይድ አፕሊኬሽን


የ አፕሊኬሽን ስም simple canner

ይህ አፕሊኬሽን በ ሀርድ ኮፒ ወይም በወረቀት ያለን በእንግሊዝኛ የተጻፈ መረጃ ወደ ሶፍት ኮፒ ይለውጣል
#አጠቃቀም
1. አፕልኬሽኑን መጫንና መክፈት
2. ስንከፍተው camera በግራ በኩል library በቀኝ በኩል ያመጣልናል
3.ስካን የተደረገ መረጃ ካለን library የሚለውን እንመርጣለን ከሌለን ደግሞ camera የሚለውን እንመርጣለን
4.camera የሚለውን ከመረጥን በኋላ ዶክመንታችንን ጥሩ ብርሃን ያለበት ቦታ ላይ አድርገን ፎቶ እናነሳዋለን
5.ከዛም የዶክመንቱን ክፍል ኣስተካክለን scan የሚለውን እንጫናለን ከዚህ ቀጥሎ የራሱ ስራ ነው ዶክመንቱን ወደ ሶፍት ኮፒ ይቀይረዋል።

#ማሳሰቢያ
ዶክመንቱ በእጅ ጽሁፍ ያልተጻፈ በኮምፒውተር regular font በእንግሊዝኛ የተጻፈ መሆን አለበት ለምሳሌ times new roman
.
.
.

Share:

Tuesday, November 1, 2016

ለመልክ ሳይሆን ለፍቅር ልኖር ይገባል!


አንድ ወቅት የአንድ ወጣት ልብ ከአንዲት በጣም
ቆንጆ መልከመልካም፤ ፀባዮ ሰናይ የሆነች ልጅ ጋር
ያርፋል፡፡
እናም ልጁ ቀረባት እሷም ቀረበችው
ተዋደዱ በጣም ተፋቀሩ፡፡ ከለታት አንድ ቀን ለዚህ አፍቃሪ ልቡን
ቀጥ
እሚያደርግ ነገር መጣ አገሩ በጥላቶች ተወረረች
መሄዱ ግድ ሆነበት ፡ ፍቅሩ ግን በእሱ ሜሄድ
ተሸበረች፡፡
ታድያ ለአገሩ ሜሄዱ ጥሩ ሁኖ እያለ ነገር ግን ጅመሩ ፍቅራቸው ሳይበስል በዛው እንዳይቀር ሰጋች፤
ፍቅሮ ለመጨረሻ
ጊዜ የመጨረሻዋን ምሽት
በጠራው ምሽት ኮዋክብት በአንድ ላይ ስለ ፍቅር
በሚዘምሩበት እና በንፋሱ ሽማግሌነት ፊት ከወደ
እግሩ በርከክ ብሎ በእጁ ትንሽ ነገር የምትመስል ነገር ግን ምግባሮ ትልቅ የሆነች ቀለበት አውጥቶ የእኔ
ቆንጆ ታገቢኛለሽ ? ብሎ ጠየቃት እሷም በ አይኖቻ
እምባ
እየወረዱ በደስታ ተቀበለችው፡፡ ወጣቱም
ላገሩ ዘመተ እሷም ብቻዋን በሃሳብና በፍቅር ተከዘች
;ታድያ ምን ያደርጋል አንድ ቀን መንገድ ላይ እየሄደች ድነገድ መኪና አደጋ ደረሰባት ፤ ያ
በውበት የቡዙ ሰው መነጋገሪያ የነበረው ውበት
በአንድ ጊዜ ተለወጠ ፤ አሁን ያቺ ቆንጆ ልጅ ሳትሆን
ፊቶ ላይ
ጠባሳ ያለባት ወደ ሚለው ተቀየረ፤
በደረሰባት አደጋ በጣም ተጎዳች አዘውትራ መጨነቅ ጀመረች እውነት የእኔ ውድ አፍቃሪ
እንደዚህ ሁኘ ልጠብቀው ፤ አይሆንም እያለች
ብቻዋን ስታወራ እናቶ ሰምታት ልጀ እንዲህማ
አትበይ አንቺ ተጨንቀሽ የምትፈጥሪው ነገር የለም
ፍቅረኛሽም
መጀመሪያ በሰላም ይምጣ እና ይወስናል ደሞ መልክ እኮ አላፊ
ነው እያለች ልታጽናናት ብትሞክር ምንም ሃዘኖ
በዛ፡፡ በዚህ ሁኔታ በዙ ግዚያት አለፉ የ ልጅቱ ኃዘን
ግን ከመበርታት በስተቀር ምንም ለውጥ የለውም ፤
ታድያ ወደ ከተማ ከመውት መኝታ ቤቶን መርጣ
በሃዠን ታሳልፋለች፡፡ አንድ ቀን መኖር አንገሸገሻት፤ አገሩን
ለቃ ልትሄድ
ወስና አልጋዋ ላይ ሁና ስታለቅስ የመኝታ ቤቱ በር
ተንኳኳ ከዛም ተከፈተ አንድ የወታደር ልብስ የለበሰ
ወጣት ከፈቶ ቆመ ደንግጣ ተነሳች ፈራች ፈቶን
በእጆቻ ሸፈነች እሱም ተይው አትሸፊኝው እኔ እንዲህ አይነት አደጋ እንደደረሰብሽ እናትሽ ፎቶ
ልካልኝ ነበር
ከለ በኋላ ከእግሩ ሸብረክ ብሎ የእኔ ቆንጆ
ታገቢኛለሽ ? አላት እሷም እኔ እኮ አታየኝም
ለአንተ አልገባም መልኬ ተበላሽቷል ስትለው እሱም
እኔ መች መልክሽን አፈቀርኩሽና አንቺ እኮ ውብና ቆንጆ የሆነ የውስጥ ውበት አለሽ ያ ለእኔ በቂ ነው
ሲላት
በአይኖቻ ዕማባዎቻ እየወረዱ ታቅፈዋለች፡፡
አያችሁ ፍቅር ሃያል ነው ሰው ለመልክ ሳይሆን
ለፍቅር ልኖር ይገባል!!


Share:

Friday, October 14, 2016

ወይ ፍቅር...!

አንድ ወጣት ፍቅረኛውን ሞተር ሳይክሉ ላይአፈናጦ በሰአት160 ኪሎ ሜትር ይከንፋል።
ልጅት፦ እባክህ ፍጥነት ቀንስ የኔ ፍቅር ፈራሁ እኮ ልጅ፦ እንድንዝናና ብዬ ነው
ልጅት፦ ኖ ፍቅር በጣም አስፈሪ ነው፤ ፕሊስ
ፍጥነት ቀንስ
ልጅ፦ እሺ እንድቀንስልሽ እንደምትወጂኝ ንገሪኝ
ልጅት፦ አፈቅርሀለሁ የኔ ቆንጆ። እሺ አሁን ቀንሰዋ
ፍቅር ልጅ፦ ሳም አድርጊኝና
ልጅት፦ ወገቡን እንቅ አርጋ እንደያዘች ሳምምምም አደረገችው
ልጅ፦ በጣም ስለሞቀኝ ሄልሜቴ ደሞ አንሺልኝና አንቺ አጥልቂው አላት። እንዳላት አደረገች።
በማግስቱ አንድ የአገሬው ጋዜጣ እንዲህ የሚል ዜና ይዞ ወጣ 
''አንድ ሞተር ሳይክል በፍሬን ብልሽት ምክንያት ተጋጭቶ ሞተሩን ሲያሽከረክር በነበረው ወጣት ላይ የሞት አደጋ ሲከሰት አብራው
የነበረች ፍቅረኛው ግን ተርፋለች።
ለካ...
ሞተሩን ያሽከረክር የነበረው ፍቅረኛዋ ድንገት ፍሬን እንደተበላሸበት ሲገባው እሷ እንዳታውቅ በማድረግ የመጨረሻ የፍቅር ቃሏን ተቀብሎ፣ የስንብት በከንፈሯ ተስሞ፣ ሄልሜቱን እሷ እንድታጠልቅ አድግርጎ፣ እሷ በህይወት
እንድትኖር ራሱን ለመስዋዕትነት እያዘጋጀ ነበር !!! እንደዚ አይነት ፍቅር ይስጠን!!!

Share:

Wednesday, October 12, 2016

ካነበብኩት ላካፍላችሁ


-ፍቅር የሚጠይቀው ብቸኛ ስጦታ "ፍቅር" ነው።
-ቅናትን እንደ ሣቅ የሚያስፈራው የለም።
-ያየውን ሁሉ ለመያዝ የሚጥር አንድ ቀን እባብ

ጨብጦ ይነደፍል።

-በአለም ላይ ከፍተኛ መራራ ነገር ቢኖር ራዕይ ማጣት ነው።
-በኢላማህ የማትተማመን ከሆነ ወደ ነብር አተኩስ።
-ብርቱካን መጨመቁን ቢያቅ ውሀ አይዝልም ነበር።
-ለማመን እንጅ ላለማመን ምክኒያት አያስፈልግም።
-በፍቅር የተነሳ ልብ በፍቅር ይሰክናል
-ቅናትን የሚፈጥረው ፍቅር ሣይሆን እራሥ ወዳድነት ነው።
-መሣሣት ሰባዊነት ሲሆን ስህተትን ማመን ጻድቅነት
ነው።
-ማለዳ ስንነሳ ልብ እንበል ከሀብት ሁሉ የሚልቅ 24
ሰዐት የኛ ነው።
-ባልና ሚስት በጋራ የሚተነፍሥ ሣንባ ባይኖራቸውም በጋራ የሚጓዝ
ሰንሰለት አላቸው።
- ሰው ጥፋቱን ሲያምን ይከበራል እንጅ
አይዋረድም።
Share:

Tuesday, October 11, 2016

ፍቅር_ማለት_????


_ፍቅር ማለት ዉበትን ፍለጋ አይደለም፣
_ፍቅር ማለት ጥቅምን ፍለጋ አይደለም፣
_ፍቅር ማለት ዝሙትን ፍለጋ አይደለም፣

_ፍቅር ማለት በደስታ ጊዜ መተቃቀፍ አይደለም፣
_ፍቅር ማለት ስለተወደዳችሁ መዉደድ አይደለም፣
#ፍቅር_ማለት ከማንነት የፀዳ
#ፍቅር ከማዳላት የራቀ
#ፍቅር ከመፍረድ እጁን ያወጣ
በመከራም በሀዘንም በደስታም መተሳሰብ መረዳዳት እናንተ ያላገኛችሁትን ነገር ለሌሎች መመኘት ፤ጠላትህን መዉደድ ፣ በናንተ እንዲፈፀም የማትፈልጉትን በሌላ ሠዉ አለመፈፀም፣ ነገ ተመልሶ በራሳችን መፈፀም አይቀርምና፣
#ፍቅር_ማለት_ይኸ_ነዉ_ለመስዋት የማይሠሥት ፍቅር መስዋትን ድል የሚያደርግ ፍቅር ይኑር በቤታችሁ!!!!
Share:

Tuesday, September 10, 2013

ፍ ቅ ር


ፍቅር ዝም ብለን የምንናገረው ቃል ወይም
የምንፅፈው ግጥም አይደለም
ፍቅር አሳብ ሳይሆን ተግባር : ስውር ሳይሆን
ግልጥ ነው
ፍቅር ወዳጅ እንጂ ጠላት ሆኖ አያውቅም
በማፍቀራችን የምናጣው ምንም ነገር የለም




Share:

ጣዕም

Featured

ፍ ቅ ር